Go to full page →

ከላይኛው ቤተ ክርስቲያን ጋር የተባበሩ መሆን፡፡ CCh 102

በታች ያለችው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በላይ ካለችው የአምላክ ቤተ ክርስቲያን ጋር አንድ ናት፡፡ በምድር ያሉ ምዕመናንና ከቶውንም ያልወደቁት በሰማይ ያሉ ፍጥረቶች አንዲት ቤተ ክርስቲያን ናቸው፡፡ በምድር እግዚአብሔርን ያመልኩ ዘንድ ጻድቃን በሚያሰርጉት ስብሰባዎች ሰማያዊ አስተዋይ ሁሉ ይደሰታል፡፡ በሰማይ በውስጠኛው ግቢ ውስጥ እነሱ በምድር ባለው በውጫዊ ግቢ ውስጥ ለክርስቶስ የሚመሰክሩትን የመስካሪዎች ምስክር ይሰማሉ ከበታችም ከሰጋጆቹ የቀረበው ውዳሴና ምስጋና ወደ ሰማያዊ መዝሙር ይወሰዳል ክርስቶስም ለወደቁት የአዳም ልጆች በከንቱ ስላልሞተ ውዳሴና ደስታ በሰማያዊ ግቢዎች ውስጥ ይስተጋባል፡፡ መላእክት ከመንጩ ራስጌ ሲጠቱ ሳለ በምድርም ያሉ ጻድቃን ከዙፋኑ ከሚፈስሉት ፈሳሾች ያምላካችንን ከተማ ከሚስደስቱት ከንጹሁ ፈሳሾች ይጠጣሉ፡፡ CCh 102.5

እረ ሁላችን ወደ ምድር የሰማይን ቅርብነት ለመገንዘብ ምነው በቻልነ! በምድር የተወለዱ ልጆች ሳያውቁት ጓደኞቻቸው የሆኑት የብርሃን መላእክት አሏቸው፡፡ ጸጥተኛው ምሥክር የሚኖረውን ነፍስ ይጠብቃለ ያነንም ነፍስ ወደ ክርስቶስ ለመሳብ ይሻል፡፡ ተስፋ እስካለ ድረስ ሰዎች ለዘላለም ጥፋታቸው መንፈስ ቅዱስን እስኪቃወሙ ድረስ እነሱ በሰማያዊ አስተዋዮች ይጠበቃሉ፡፡ እንግዲህ በታች ጻድቃን በሚያደርጉት ስብሰባ ሁሉ ያምላክ መላእክት የሚያቀርቡትን ምስርነት መዝሙሮችና ጸሎቶች የሚያዳምጡ እንዳሉ ሁላችን በሐሳባችን እንጠብቅ፡፡ CCh 103.1

እንግዲህ ከሰንበት ወደ ሰንበት ስንገናን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ ለጠራህ የምስጋናዎች መዝሙር ዘምር፡፡ ‹‹ለወደደነ ከኃጢአትታችንም በደሙ ላጸበነ›› የልብ ስግደት ይሰጠው፡፡ የክርስቶስ ፍቅር የተናጋሪው ንግግር ሸክም ይሁነለት፡፡በምስጋና መዝሙ ሁሉ በተስተዋለ አነጋገር ይገለጽ፡፡ ጸሎታችሁን ያምላክ መንፈስ ይምራው፡፡ የሕይወት ቃል ሲነገር ከልብ የተሰማህ መልስ ከሰማይ መልእክት የምትቀበል መሆንህን ይመስክር፡፡ CCh 103.2

እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ የፍቅር ጠባ እናበጅ ዘንድ በቤቱ እንድንሰበሰብ ስተምረናል፡፡ ይህም ክርስቶስ ለሚወዱት ሊያዘጋጅላቸው ስለ ሔደው የምደርን ነዋሪዎች ተገቢዎች ያደርጋቸዋል፡፡ እዚያ እጅግ ከፍ ባለው የመዝሙር ዜማዎች በዙፋን ላይ ለሚቀመጠውና ለዘላለምና ለዘላለም ለበጉ ውዳሴና ምስጋና በማቅረብ ይተባበሩ ዘንድ ከሰንበት ወደ ሰንበት ከአዲሱ ጨረቃ ወደ ሌላው በመቅደስ ውስጥ ይሰበሰባሉ፡፡46T36-368; CCh 103.3