Go to full page →

በእግዚአብሔር ቤተ ጸሎት የሚደረግ የጸሎት ሥነ ሥርዓት፡፡ CCh 113

ሰጋጆቹ ወደ ጸሎት ሥፍራ ሲገቡ በከበሬታ ወደ መቀመጫዎቻቸው በጸጥታ እያለፉ መጸለይ አለባቸው፡፡ በክፍሉ ውስጥ ምድጃ ካለ በስንፍና ባለ መጠንቀቅ ምድጃውን ከብቦ መያዝ ተገቢ አይደለም፡፡ ተራ ንግግር ማሾክሾክና መሳቅ በቤተ ጸሎት ውስጥ ቀደም ብሎ ወይንም ከጸሎት አገልግሎት በኋላም ቢሆን ሊፈቀድ አይገባም፡፡ የጋለ ከልብ የሆነ ጸሎት ሰጋጆቹ መጸለይ አለባቸው፡፡ CCh 113.3

ጸሎቱ ከመጀመሩ በፊት አንዳንዶቹ ጥቂት ደቂቃዎች መቆየት ካለባቸው በጽሞና ሐሳብ በጸሎት ልብን ወደ እግዚአብሔር እያነሱ እውነተኛ የሆነ የጸሎት መንፈስ ይኑራቸው አገልግሎቱ ለገዘ ልባቸው የተለየ ጥቅም እንዲሆንና ሌሎችን ነፍሳት ወደ ማሳመንና ወደ መመለስ ይመራቸው ዘንድ፡፤ ሰማያዊ መልእክተኛች በቤት ውስት እንዳሉ ማሰብ አለባቸው፡፡ ዕረፍተቢሶች በመሆናችን የማሰብንና የጸሎት ጊዜያትን ባለማጥበቃችን ሁላችን ከአምላክ ጋር ጣፋጭ የሆነ ግንኙነት በጣም እናጣለን፡፡ መንፈሳዊ ሁኔታችን ብዙ ጊዜ ልንመራመርበትና ሐሳባችንና ልባችን ወደ ጽድቅ ጸሐይ ሊሳብ ያስፈልጋል፡፡ CCh 113.4

ሕዝቡ ወደ ቤተ ጸሎት ሲመቱ ለጌታ ዓይነተኛ ከበሬታ ቢሰጡና በፊቱ መሆናቸውንም በሐሳባቸው ትዝ ቢላቸው በዝምተኝነታቸው ጣፋጭ የሆነ አፈ ጮሌነት ይሆንባቸዋል፡፡ ኃጢአት ያልሆነም በተለመደው የሥራ ቦታ የሚነጋገሩት ማሾክሾክ፣ መሳቅና ንግግር አምላክ በሚመለክበት ቤት ውስጥ መጽደቅ የለበትም፡፡ ሐሳብ የሚገባ ሚዛናዊ ክብደት ኑሮት ለልብ እንደሚስማማው ያሳትፍለት ዘንድ ያምላክን ቃል ለመስማት መዘጋጀት አለበት፡፡ CCh 113.5

ሰባኪው ሲገባ ግርማ በሚሰጠው በእርጋታ ሁናቴ መሆን አለበት ወደ አትሮኑ (ፑልፒት) ወዲያው እንደ ተራመደ በጽሞና ጸሎት ጎንበስ ብሎ ከልብ ከአምላክ እርዳታ መለመን አለበት፡፡ ይህ እንዴት ያለ ሐሳብ ያሳትፍ ይሆን! በሕዝቡ ዘንድ ከበሬታና ፈሪሀ እግዚአብሔርን ያሳድርባቸዋል፡፡ ሰባኪያቸው ከአምላክ ጋር መነጋገሩ ነው በሕዝብም ፊት ለመቆም ከመድፈሩ በፊት ራሱን ለአምላክ አደራ መስጠቱ ነው፡፡ በሁሉመ ላይ ከበሬታ ያርፍባቸዋል አምላክም መላእክት በጣም ይቀርቡዋቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ጸሎቱን እዚያ በመገኘቱ እንዲባርከውና ከሰብዓዊ ከናፍር ለተነገረው እውነት ኃይል እንዲሰጥ አምላክን የሚፈሩ ጉባኤ ሁሉ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ከርሱ ጋር በጽሞና ጸሎት ይተባበሩ፡፡ 15T 191 - 493; CCh 114.1

ለኮንፈረንስ (ለጉባዔውና) ለጸሎት የተወሰኑት ስብሰባዎች አስልቻቾት ሊሆኑ አይገባም፡፡ ከተቻለ ሁሉም ልክ በተወሰነው ሰዓት መገኘት አለባቸው፡፡ ጊዜውን አሳልፈው ግማሽ ሰዓት ወይንም አሥራ አምስት ደቂቃዎች እንኳ ቢሆን የሚዘገዩ ሰዎች እንዳሉ እነሱን መቆየት ተገቢ አይደለም፡፡ ሁለት ብቻ ካሉ ተስፋውን ሊለምኑ ይችላሉ፡፡ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች ቢኖሩም ከተቻለ ስብሰባው በተወሰነው ሰዓት መከፈት (መጀመር) አለበት፡፡ 22T577, 578; CCh 114.2