እናት የምታጠባውን ልጂን ልትረሳ ትላለችን?
ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ
ይሆናል፤ እኔ ግን አልረሳም። እነሆ በእጁ መዳፍ
ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው፡፡
ኢሳ 49፡15-16
ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፡፡
ዮሐ 6፡37
የክርስቶስ ብርታት ሊያወጣት ከማትችልበት አዘቅት ውስጥ የገባች ነፍስ የለችም፡፡ ... በችግር ውስጥ ያላች ነፍስ የምታሰማው ቃላት-ያጠረው ጩኸት በጌታ ዘንድ ሳይሰማ አይቀርም፡፡ ከሰማይ አምላክ ጋር የኪዳን ግንኙነት ለማድረግ የተስማሙ ሁሉ ለሰይጣን ኃይል ወይም ለራሳቸው የተፈጥሮ ድካም አይተውም፡፡ እቃገ 35.1
ራሳችሁን እስክታሻሽሉ፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ወደሚያስችል መልካምነት እስክትደርስ ድረስ ከክርስቶስ እንድትርቁ ጠላት የሚያቀርብላችሁን አሳብ አትቀበሉ፡፡ያ እስኪሆን የምትጠብቁ ከሆነ መቼም ወደ ክርስቶስ አትመጡም፡፡ ሰይጣን ወደ መርገም ጨርቃችሁ ሲጠቁማችሁ፣ “ወደ እኔ የሚመጣውን ወደ ሜዳ አልሰደውም” ዮሐ 6፡37 ሰማላት ጌታ የተናገረውን የተስፋ ቃል ድገሙለት፡፡ እቃገ 35.2
በእግዚአብሔርና በእያንዳንዷ ነፍስ መካከል ያለው ግንኙነት ልክ በምድር ላይ የእርሱን ጥብቃ የምትጋራና የተወደደውንም ልጁን የሰጣት ሌላ ነፍስ የሌላ ይመስል የተሟላና የግል ነው፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን ዘወትር ሰይጣን በጥንቃቄ ወደ እርሱ ሊደርስ የሚችልበትን መንገድ ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ለመለኮታዊ ኃይል ሊጸልይ እንዲሁም ወደ ኃጢአት የሚጎትተውን ዝንባሌ ሁሉ በጽናት ሌቋቋም ይገባል፡፡ ኃጢአት ለመስራት በሚመርጡበት ጊዜ ሰዎች ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ይነጥላሉ፤ ከበረከት አሸንዳ ራሳቸውን ያለያያሉ፤ የመጨረሻ ውጤታቸውም ጥፋትና ሞት ነው፡፡ እቃገ 36.1
የአዳኙ በመለኮታዊ ፍቅር የተሞላ ልብ፣ ከሌሎች ሁሉ በጠላት ወጥመድ ውስጥ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ሁኔታ ተቆላልፎ ወደሚገኘው ነፍስ በበለጠ በርህራሄ ይሳባል፡፡ እግዚአብሔር ከኃጢአታችን የተነሳ አሳልፎ አይሰጠንም፡፡ ስህተት ልንሰራ እንችላላን፤ መንፈሱንም እናሳዝን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ንስሓ ስንገባ፣ በተሰበረም ልብ ወደ እርሱ ስንቀርብ ፈጽሞ ፊቱን አያዞርብንም፡፡ እቃገ 36.2
እረኛ በጎቹን እንደሚወድ ፣ አንድ በግ እንኳ ቢጎድልበት አርፎ እንደማይቀመጥ እግዚአብሔርም ወሰን በሌለው ፍቅሩ እያንዳንዷን የተገለለች ነፍስ እንደዚያው ይወዳል፡፡ የእርሱ ፍቅር “የእኔ ናችሁ” ሲላቸው ሰዎች ላይቀበሉ ይችላሉ፤ ከእርሱ በመሽሽ ሌላ ጌታ ሊመርጡ ይችሉ ይሆናል፤ ያም ሆኖ ግን እነርሱ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ጌታም እንደገና የራሱ ሊያደርጋቸው ይመኛል። እቃገ 36.3
ያለፈ ታሪካችሁ ምንም ቢሆን ምን፣ ወቅታዊ ሁኔታችሁ ምንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ሲሆን፣ ልክ እንዳላችሁ ሆናችሁ ከነድካማችሁ፣ ረዳተቢስነታችሁና ሃዘናችሁ ወደ ኢየሱስ ብትመጡ ሩህሩህ አዳኛችን ገና ከሩቅ ሳላችሁ ይቀበላችኋል፤ የፍቅር እጆቹንም ዘርግቶ ይጠመጠምባችኋል፤ የጽድቅ ልብሱንም ያለብሳችኋል፡፡ እቃገ 36.4