Go to full page →

አንድም እንቢ አልተባለም CLAmh 150

ስለ የሱስ የተባለውን ሁሉ ያሰላስል ነበር፡፡ ማንም የየሱስን እርዳታ ፈልጎ አልተነፈገውም፡፡ ያ ጎስቋላ ሰው መድኅንን ሊገናኝ ፈለገ፤ ቆረጠም፡፡ ከከተማ ውጭ እንዲኖር ቢገደድም እንደምንም ብሎ ከከተማ ውጭ ወይም በተራራ ላይ ሲያስተምር ሊያገኘው ፈለገ፡፡ ብዙ ችግር ቢኖርበትም ተስፋው በየሱስ ላይ ብቻ መሆኑ ገባው፡፡ CLAmh 150.4

ከሩቅ ቆሞ ከየሱስ ንግግር አንዳንዱን ይሰማ ነበር፡፡ የሱስ እጁን በበሽተኞች ላይ ሲጭን አየው፡፡ አንካሶች፣ ዕውራን፣ ሽባዎች፣ በአጋንንት የተያዙ ሁሉ ሙሉ ባለጤኖች ሆነው ከሞት ሲድኑ ተመለከተ፡፡ ያን ጊዜ ሃይማኖቱ ጸና፡፡ ቀስ በቀስ ወደ ጉባዔው ቀረበ፡፡ የተጣለበት ገደብ (መታገድ) የሕዝቡ ደኅንነት፤ ሰዎች ስለራሱ የሚሠነዝሩበት ምፀትና አሽሙር ሁሉ ተረሳው፡፡ ያን ጊዜ ያስብ የነበር ስለተባረከው የመዳን ተስፋ ብቻ ነበር፡፡ CLAmh 150.5