Go to full page →

ለከፍተኛ ቦታ መጠራት CLAmh 195

ብዙ ሰዎች ራሣቸውን ማሻሻል ስለማይችሉ በተሳሳተ መንገድ ይጓዛሉ፡፡ ግን እንደዚህ ማድረግ የለባቸውም፡፡ የቻሉትን ያህል ከፍተኛ አገልግሎት ካበረከቱ ምንጊዜም ለሥራ ይፈለጋሉ፡፡ CLAmh 195.1

ለሚፈልጉበት ሥራ ከፍተኛ ግምት ይሰጣቸዋል፡፡ ሰዎች ለከፍተኛ ኃላፊነት ብቁ ሆነው ቢገኙ እግዚአብሔር ኃላፊነቱን በእነርሱ ላይ ብቻ አይጭነውም፤ ግን ከሚያውቋቸውና ከፍተኛ ግምት ከሰጣቸው ጋር ያካፍላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለከፍተኛ ደረጃ የሚጠራቸው የተጣለባቸውን የየዕለት ተግባራቸውን በየቀኑ የሚያከናውኑትን ነው፡፡ CLAmh 195.2

በቤተልሄም ኮረብታዎች በጎቻቸውን ይጠብቁ የነበሩትን እረኞች መላእክት ጎበኙአቸው፡፡ ዛሬም ቢሆን ዝቅተኛው ሠራተኛ የዕለት ተግባሩን ሲያካሄድ መላእክት የሚናገረውን ቃል እያዳመጡ የሥራውን ዓይነት እየተመለከቱ ከአጠገቡ አይርቁም፡፡ የሥራውን ይዞታ በመመልከት ለከፍተኛ ኃላፊነት ብቁ መሆን አለመሆኑን ይወስናሉ፡፡ CLAmh 195.3

እግዚአብሔር ሰዎችን የሚገምታቸው በሀብታቸው ማነስና መብዛት፤ በመማርና ባለመማራቸው፤ ወይም በሥልጣናቸው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን የሚለካቸው በአሳባቸው ቅንነትና በጠባያቸው ጨዋነት ነው፡፡ ምን ያህል መንፈስ እንዳደረባቸውና በጠባያቸው ምን ያህል እርሱን እንደሚመስሉ ይመለከታል፡፡ CLAmh 195.4

በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ለመሆን እንደ ህፃን ገር መሆን ያሻል፡፡ በፍቅርና በሀይማኖትም የሕፃንን ቅንነት ማሳየት ተገቢ ነው፡፡ CLAmh 195.5

ክርስቶስ ፣ “የአህዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆችም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ ፤ በእናንተስ እንዲሁ አይደለም፡፡ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን ቢወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን” አለ፡፡ (ማቲዎስ 20፡26) CLAmh 195.6