Go to full page →

ስለ እግዚአብሔር ተስፋዎች ተናገር CLAmh 203

ስለ እግዚአብሔር ተስፋዎችና የሱስ ሊባርከን ፈቃደኛ ስለመሆኑም ተናገር፡፡ ለአንድ አፍታ እንኳን ቢሆን አይረሳንም፡፡ በችግር ጊዜም ቢሆን በእርሱ በመመካት አምነን ካረፍን ልባዊ ደስታ ይሰማናል፡፡ ስለ አብ ክርስቶስ ሲናገር “አባቴም እንደ አስተማረኝም እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያ ጊዜ ታውቃላችሁ፡፡ የላከኝንም ከእኔ ጋር ነው ፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም” ይላል፡፡ (ዮሐንስ 8፡28፣29) CLAmh 203.3

አብ ከወልድ ስላልተለየ የሚሠራው ሁሉ ከአብ ፈቃድ ውጭ አልነበረም፡፡ የእርሱ ብርታት ምክንያቱ ይህ ነበር የእኛም ያው ነው፡፡ የክርስቶስ መንፈስ ያረፈበት ሰው ከክርስቶስ ጋር ይኖራል፡፡ የሚያገኘው ሁሉ ከማይለየው ከመድኃኒታችን ዘንድ ነው፡፡ በአምላክ ፈቃድ ካልሆነ በቀር ምንም አይነካውም፡፡ CLAmh 203.4

ሥቃያችንና ኀዘናችን፤ ፈተናችንና መከራችን፤ ትካዜያችን ሁሉ ስደትና መገላታታችን ሁሉ፤ በአጭሩ ማንኛውም ነገር ለመልካም ይሆናል። ማንኛውም አጋጣሚና የኑሮ ድርሻ ለእኛ ሲል እግዚአብሔር ያዘጋጃልን ዝግጅት ነው። CLAmh 203.5

እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ትግስት ካስተዋልን በሌሎች ላይ መወንጅል ባላበዛንም ነበር። CLAmh 203.6

ክርስቶስ በዚህ ምድር ሳለ ተክታዮቹ ማንነቱን ካወቁ በኋላ አንዲት ስድብ ቃል ወይም የቁጣ ንግግር ቢስሙብት ኖሮ እንዴት በተደነቁ ። የሚወዱትን ሁሉ የእርሱን ጠባይ መውርስ እንዳለባቸው አንዘጋ። CLAmh 203.7

“በወንድማሞች መዋደድ እርሰ በእርሰችሁ ተዋድዱ ፤ እርሰ በእርሰችሁ ተከባበሩ።” (ሮሜ 1፡9)” ክፉን በክፉ ፋንታ ወይም ስድብን በስድብ ፋንታ አትመልሱ ፤ በዚህ ፋንታ ባርኩ እንጂ። በረከት ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኃል። “(1ኛጴጥሮስ 3፡9) CLAmh 204.1