Go to full page →

የቤተሰብ ሕግ ደንጋጊ CLAmh 34

የቤተሰቡ ሕግ ደንጋጊ አባትየው ነው፤ አብርሃም እንዳደረገው የቤተሰቡ መመሪያ ደንብ የእግዚአብሔር ሕግ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ስለ አብርሃም “ጽድቅና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና” ይላል፡፡ ዘፍ 18፡19፡፡ ኃጢአትን ለመከላከል ችላ አይልም፤ ማዳላት ሊኖር አይገባም፤ ትክክል ባልሆነ ፍቅር ምክንያት ኃላፊነቱን ችላ ማለት የለበትም፡፡ አብርሃም ማስተማር ብቻ ሳይሆን ራሱ ትክክለኛውን ሕግ ጠበቀ፡፡ እግዚአአብሔር ለኛ መመሪያ የሚሆን ደንብ ሰጥቷል፡፡ ልጆች እግዚአብሔር ካዘጋጀው ትክክለኛ መንገድ ወጥተው አስጊ በሆነ ጐዳና ላይ መንከራተት የለባቸውም፡፡ በፍቅር፤ ባለማወላወል፤ ባለመሰልቸትና በጸሎት የልጆች ስሕተት መታረምና ትክክል ያልሆነው ፍላጎታቸው መወገድ አለበት፡፡ CLAmh 34.2

አባትዮው ቤተሰቦቹ ታማኞች፣ ትዕግስተኞች፣ ደፋሮች፣ ትጉሆችና ጠቃሚዎች እንዲሆኑ ማድረግ አለበት፡፡ ልጆች እንዲያደርጉ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ እርሱ ራሱ አድርጎ ማሳየት አለበት፡፡ CLAmh 34.3

አባቶች ሆይ፤ ልጆቻችሁን ተስፋ አታስቆርጡ፡፡ ከሥልጣናችሁ ጋር ፍቅር፤ ከጥብቅነታችሁ ጋር ርኅራኄ ይቀላቀልበት፡፡ ልጆቻችሁ እንዲተማመኑባችሁ በእረፍት ጊዜአችሁ አብራችኋቸው ሁኑ፤ በሥራና በጨዋታቸው ጊዜ አትለይዋቸው፡፡ በተለይ ከወንዶች ልጆቻችሁ ጋር ጓደኝነት ይኑራችሁ፡፡ በዚህ አኳኋን ወደ ጥሩ ነገር ልትመሯቸው ትችላላችሁ፡፡ CLAmh 34.4

አባትዮው በተቻለው መጠን ቤተሰቡን የሚያስደስት መሆን አለበት፡፡ ምንም ዓይነት ችግር ወይም የሥራ ጣጣ የቤተሰብ ኃላፊነትን ሊያስጥለው አይገባም፡፡ ወደ ቤቱ ሲገባ በፊቱ ላይ ፈገግታ ሊታይ አስደሳች ቃላት ሊናገር ይገባዋል፡፡ CLAmh 34.5