Go to full page →

አዲስ የአበላል ልምድ CLAmh 54

በጣም ጣፋጭ የሆነ ምግብ መብላት የለመዱ ሰዎች የምግብ አምሮታቸው የተቃወሰ ነው፤ በጣም የሚጣፍጥ ነገር ያተቀላቀለበት ምግብ ለመብላት አይችሉም፡፤ የምግብ አምሮታቸውን ለማረምና መጥፎ የለመደውን ጨጓራቸውን ወደ ተፈጥሮው ልምዱ ለመመለስ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ትክክለኛውን ምግብ መብላት የለመዱት ግን ጣፋጭ ነገር ያልበዛበት ምግብ መብላት አያዳግታቸውም፡፡ በቀላሉ የተሠራ ለአካላችን ተስማሚ የሆነውን ምግብ ጨጓራችን በቀላሉ ይፈጨዋል፡፡ CLAmh 54.3

በጤና ለመኖር ለአካላችን ተስማሚ የሆነ በቂ ምግብ ያስፈልጋል፡፡ በደንብ ከታሰበበት ለጤና የሚስማማ ምግብ በየአገሩ ይገኛል፡፡ ሩዝ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ አጃ፣ ባቄላ፣ አተርና ምስር በልዩ ልዩ አኳኋን እየተዘጋጁ ወደ ውጭ አገር ይላካሉ፡ እነዚህን ጥራጥሬዎች ከፍራፍሬና ከአትክልት ጋር አቀላቅሎ በመብላት ያለ ሥጋ የተሟላ ምግብ ለማግኘት ይቻላል፡፡ CLAmh 54.4

ፍራፍሬ በብዛት ከሚገኝበት ቦታ ፍሬ ለማይገኝበት ጊዜ በቆርቆሮ አሽጎ ማስቀመጥ ተገቢ ነው፡፡ እንደ ጐስቤሪ፣ ስትሮበሪ፣ ራስቤሪና ብላክቤሪ ያሉ ጥቃቅን ፍሬዎች በብዙ ልዩ ልዩ ቦታ ሊበቅሉ ይችላሉ፡፡ CLAmh 55.1

በቆርቆሮ የሚታሸግ ፍሬ ጤነኛ መሆን አለበት፡፡ ከጥቂት ስኳር ጋር ፍሬውን እንዳይበላሽ አድርጎ መቀቀል ነው፡፡ በእንደዚህ ያለ አኳኋን ከተዘጋጀ እንደ አዲስ ፍሬ ይጠቅማል፡፡ CLAmh 55.2

እንደ ዘቢብ፣ አፕል፣ ኮክና አፕሪኮት ያሉ ፍሬዎች በመጠነኛ ዋጋ ከተገኙ አዘውትሮ በመብላት ጤናን ለማሻሻልና ብርታትን ለማግኘት ይቻላል፡፡ CLAmh 55.3