Go to full page →

ለምግብ የሚያገለግሉ እንስሳት በሽታ CLAmh 63

ሥጋ ከጥንትም መልካም ምግብ አይደለም፤ አሁን በተለይ የእንስሳት በሽታ አየተራባ ሲሄድ ምግብነቱ በበለጠ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሥጋ የሚመገቡ ሰዎች ስለምግባቸው የሚያውቁት ነገር የተወሰነ ነው፡፡ ሁልጊዜ ለእርድ የሚቀርቡትን እንስሳት ቢያዩና የሚበሉትን የሥጋ ጥራት ቢያውቁ ኖሮ ሥጋ መብላት በዘገነናቸው ነበር፡፡ ሰዎች የሚበሉት ሥጋ አብዛኛውን በካንሰርና በሳንባ ነቀርሳ ጠንቆች የተበከለ ነው፡፡ ስለዚህ በምግቡ አማካይነት ካንሰርንና የሳንባ ነቀርሳን የመሳሰሉ ለሞት የሚያደርሱ የበሽታ ዓይነቶች ወደ ተመጋቢው ይተላለፋሉ፡፡ CLAmh 63.4

የአሳማ የአካል ክፍሎች በተውሳክ የተሞሉ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ስለ አሳማ እንዲህ ይላል፡፡ “ሥጋውን አትብሉ፤ በድኑንም አትንኩ” ይላል፡፡ (ዘዳግም 14፡10) ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው የአሳማ ሥጋ ለምግብነት ተስማሚ ባለመሆኑ ነው፡፡ ምንም ቢሆን ሥጋውን ሰብአዊ ፍጡር ሊቀምሰው አይገባም፡፡ አሳማዎች ቆሻሻ አጣሪዎች ናቸው፡፤ አገልግሎታቸውም ይኸው ብቻ ነው፡፡ ምግቡ ቆሻሻ፣ ኑሮው አስጸያፊ የሆነ እንስሳ ሁሉ ሥጋው ጤናማ ነው ማለት ዘበት ነው፡፡ CLAmh 63.5

አብዛኛዎቹ ከብት ሻጮች የታመሙትንና የከሱትን፤ መኖራቸው ያሠጋቸውን ከብቶቻቸውን ለገበያ ያቀርባሉ፡፡ ለገበያ ለማቅረበ በሚደረገው የማወፈር ጊዜ እንስሳቱ በሽታ ሊያፈሩ ይችላሉ፡፡ CLAmh 63.6

ንጹህ አየር እንደልብ በማይገኝበት ክፍል ሲዘጋባቸው፤ የቆሻሻውን በረት አየር ሲስቡ፤ ምናልባትም የበሰበሰ ምግብ ሲቀርብላቸው፤ አካላቸው በሙሉ በበሽታ ይበከላል፡፡ እንስሳቱ ወደ ገቢያው ለመድረስ ረዥም ጎዳና ያቋርጣሉ፤ ብዙ ሥቃይም ይደርስባቸዋል፡፡ CLAmh 64.1

ከለምለም መስክ ይወገዳሉ፤ በሞቃትና በአድካሚ መንገድ ላይ ይጓዛሉ፤ ወይም በቆሻሻ መኪና ውስጥ ይታጨቃሉ፡፡ ለብዙ ሰዓታት ምግብና ውኃ ስለሚቀርባቸው ይዝላሉ፤ ሰዎች በድናቸውን እንዲመገቡ ምስኪኖቹ እንስሳት ወደ ሞት ይነዳሉ፡፡ CLAmh 64.2

በብዙ ቦታዎች ዓሣዎች በሕመም ስለሚለከፉ ለሚበሏቸው ሰዎች የበሽታ ጠንቅ ይሆናሉ፡፡ በተለይ የከተማ ቆሻሻ መፋሰሻ በሆኑት ወንዞች ውስጥ የሚገኙት ዓሣዎች ምግብነታቸው በበለጠ ያሰጋል፡፡ በዚያ በተበከለ ውኃ የሚኖሩት ዓሣዎች ብዙ ርቀት አቋርጠው ንጹህ በሆነ ውኃ ውስጥ ሊያዙ ይችላሉ፡፤ ስለዚህ ተይዘው ሲበሉ አደጋውን ባልጠረጠሩት ተመጋቢዎች ላይ በሽታን ያመጣሉ፡፡ CLAmh 64.3