Go to full page →

ተስማሚ ልብስና የሰውነት (የአካል) ማጠንከሪያ ልምምድ CLAmh 73

ጤናቸው የታወከ ሴቶች በተስማሚ ልብስና በአካል ማጠንከሪያ ልምምድ አማካይነት ጤናቸውን ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡ ከቤት ውጭ ለሽርሽር ሲወጡ በሚገባ ለብሰው በሜዳ ላይ ልምምዳቸውን ይቀጥሉ፡፡ መጀመሪያ በጥንቃቄ በመለማመድ እየቆዩ ልምምዳቸውን መጨመር ይችላሉ፡፡ ይህን የተጣለባቸውን የሥራ ድርሻ ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡ CLAmh 73.4

ሴቶች ከፋሽን ጋር ግብ ግብ በመግጠም ፋንታ ለጤናቸው ተስማሚ የሆነና ቀላል ልብስ መልበስ ይሞክሩ፡፡ እንዲሁ ከቤት ሥራ ጋር መዳረቅ ብቻ ሳይሆን የቤት እመቤት መጽሐፍ ታንብብ፤ ዕውቀቷን ታዳብር፤ ባሏን ትርዳ፤ የልጆቿን አእምሮ ኮትኩታ ታሳድግ፡፡ የተወደዱ ልጆቿን ለከፍተኛ ሕይወት ለማዘጋጀት የተሰጣትን መብትና ግዴታ ትሥራበት፡፡ የተወደደውን መድኅን የቅርብ ወዳጅና የየዕለት ባልደረባ አድርጋ ትቁጠረው፡፡ ቃሉን ታጥና፤ ልጆቿን ወደ ውጭ ወስዳ ማንሸራሸር አትርሳ፡፡ በተፈጥሮ ውበት አማካይነት ስለእግዚአብሔር ታስተምራቸው፡፡ CLAmh 74.1