Go to full page →

የጥረት ተፈላጊነት CLAmh 89

በመጥፎ አመል የተለከፉ ሰዎች ራሳቸው ለራሳቸው መጣር አለባቸው፡፡ ሌሎች የቻሉትን ያህል ሊረዱአቸው ይታገሉ ይሆናል፡፡ የእግዘአብሔር ጸጋ ይታደልላቸው ይሆናል፡፡ ክርስቶስም መላእክቱን ልኮ እንዲረዱአቸው ያደርጋል፡፡ CLAmh 89.3

ግን ራሳቸው ለራሳቸው ካልተዋጉ የሚደረገው ጥረት ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ ሰሎሞን ወጣት ሳለ መንግስቱን ሊወርስ ሲል ዳዊት “በርታ ሰውም ሁን” አለው፡፡ (1ኛ ነገሥት 2፡2) ፡፤ ሰብዓዊ ዘር ሁሉ የማይጠፋ ዘውድ ሊደፉ ሲሉ “በርቱ ሰዎችም ሁኑ” ይባላሉ፡፡ CLAmh 89.4

ራሳቸውን መግታት ላቃታቸው ሁሉ የግብረ ገብ ቅድስና ተፈላጊነት ሊብራራላቸው ይገባል፡፡ በኃጢአት ኑሮ የለወጡት ሰውነታቸው እግዚአብሔር በክርስቶስ ብርታት እንዲመለስላቸው ይፈልጋሉ፡፡ CLAmh 89.5

የፈተናን መክበድ የሚመለከቱ ብዙ ሰዎች “ክፉን ማሸነፍ አንችልም” በማለት ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ እንደሚችሉና ሊቋቋሙትም እደሚገባቸው ንገሩአቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ተሸንፈው ይሆናል፤ ግን እንደተሸነፉ አይቀሩም፡፡ ሞራሉ የተዳከመው በኃጢአት ልምድ ስለተጠቃ ነው፡፡ ተስፋውና ውሳኔው የአሸዋ ክምር ሆኖበታል፡፡ ተስፋውን እንዳልጠበቀና ቃሉን እንዳላከበረ ስለሚያውቅ በራሱ ላይ ያለው ዕምነት ይዳከምበታል፡፡ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ጥረቱን የማይቀበልለትና በትግሉም የማይረዳው ይመስለዋል፡፡ ግን ተስፋ መቍረጥ አያስፈልገውም፡፡ CLAmh 89.6