Go to full page →

መዳን ለሁሉ ወገን CLAmh 129

ክርስቶስ የወንጌልን መልዕክት ለማዳረስ ያገኘውን ዕድል ሁሉ ከሥራ ላይ ያውለው ነበር፡፡ ለዚያች ሳምራዊት ሴት የተናገረውን ግሩም ቃል ተመልከቱ፡፡ ሴትዮዋ ውኃ ልትቀዳ ስትመጣ በያዕቆብ ጉድጓድ አጠገብ ተቀምጦ ነበር፡፡ አንድ ነገር እንድታደርግለት ሲጠይቃት ተገረመች፡፡ “የምጠጣው ስጭኝ” አላት፡፡ ቀዝቃዛ ውኃ አሰኝቶት ነበር፤ ለእርሷም የሕይወትን ውኃ ሊያጠጣት ፈለገ፡፡ “አንተ የአይሁድ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆነው ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም” አለችው፡፡ የሱስም “የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ አንች ትለምኚው ነበርሽ፤ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር” አላት፡፡ ንግግሩንም በመቀጠል “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘላለም አይጠማም፤ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ” አለ፡፡ ዮሐንስ 4፡7-14፡፡ CLAmh 129.6

ለዚች አንዲት ሴት ክርስቶስ እንዴት አሰበላት! ንግግሩ ቁም ነገር ያለበትና በደንብ የተቀነባበረ ነበር፡፡ ይህን ከሰማች በኋላ ሴትዮዋ እንስራዋን ትታ ወደ መንደር ስትሮጥ ሄደች፡፡ ለጎረቤቶቿም “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆን?” አለች፡፡ የሰማርያም ሰዎች ብዙ አመኑበት” ዮሐንስ 4፡29-39 CLAmh 130.1

ከዚያ ዘመን ጀምሮ እነዚህ ቃላት የመለሱትን ነፍሳት ብዛት ማን ሊገምት ይችላል፡፡ ሰዎች ትምህርቱን ለመቀበል ዝግጁ ከሆኑ ክርስቶስ ምን ጊዜም ለማስተማር ዝግጁ ነበር፡፡ አብን ያስተዋውቃቸዋል፤ ልብን መርምሮ የሚያውቀው አምላክ ምን እንደሚያስደስተው ይነግራቸዋል፡፡ እንደዚህ ላሉት በምሳሌ አላስተማረም፡፡ በውኃው ጉድጓድ ላገኛት ሴት እንዳለው ለእነርሱም “እርሱ እኔ ነኝ” ይላቸዋል፡፡ ዮሐንስ 4፡26 CLAmh 130.2