የውርስ ኃይል።--የውርስን ኃይል፣ የክፉ ሕብረቶችንና አካባቢዎችን ተጽእኖ፣ የመጥፎ ልምዶችን ኃይል ከግምት ውስጥ ያስገቡ። ከእንደዚህ ዓይነቶች ተጽእኖዎች የተነሣ ብዙዎች መዋረዳቸው ያስገርመናልን? እነርሱን ከፍ ለማድረግ ለሚደረጉ ጥረቶች ምላሽ ለመስጠት በማዝገማቸው (ቀስ በማለታቸው) መገረም እንችላለንን? --MH 168 (1905). {1MCP 142.1} 1MCPAmh 116.1
ልጆች ብዙ ጊዜ ባሕርይን ይወርሳሉ።--እንደ ደንብ ስንወስድ ልጆች የወላጆቻቸውን ባሕርያትና ዝንባሌዎችን ስለሚወርሱና ምሳሌያቸውን ስለሚቀዱ የወላጆች ኃጢአቶች በልጆች ከትውልድ እስከ ትውልድ ይተገበራሉ። በዚህ መልኩ የካም ከንቱነትና አክብሮት ማጣት በዘሩ እየተባዛ ከመሄዱ የተነሣ ለብዙ ትውልዶች እርግማን አምጥቶባቸዋል።… {1MCP 142.2} 1MCPAmh 116.2
በሌላ በኩል ሴም ለአባቱ የነበረው አክብሮት ያስገኘለት ሽልማት ምንኛ መልካም ነበር፤ በእርሱ ዝሪያዎች ውስጥ የተገኘው ምንኛ ስመ-ጥር የሆኑ ቅዱሳን ሰዎች የዘር ሀረግ ነበር! --PP 118 (1890). {1MCP 142.3} 1MCPAmh 116.3
እናቶች የውርስ ሕጎችን በተመለከተ ለራሳቸው እውቀት ማግኘት አለባቸው።--ባለፈው ትውልድ እናቶች ስለ አካላቸው ሕጎች እውቀት አግኝተው ቢሆን ኖሮ የአካል ጥንካሬያቸውም ሆነ የግብረገባቸውና የአእምሮ ክፍሎቻቸው ቅኝት በልጆቻቸው ላይ በከፍተኛ ደረጃ ይታይ ነበር። ይህን ያህል ብዙ ነገርን በሚያካትት በዚህ ርዕስ ላይ እውቀት ማጣታቸው ወንጀል ነው።--HL (Part 2) 37, 1865. (2SM 431.) {1MCP 142.4} 1MCPAmh 116.4
ከወላጆች ወደ ልጆች የተላለፉ በሽታዎች።--ከውድቀት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ትውልዶች የሚታየው ዝንባሌ በቀጣይነት ቁልቁል የሚሄድ ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ በሽታዎች ከወላጆች ወደ ልጆች ሲተላለፉ ቆይተዋል። በሕጻን አልጋ ላይ ያሉት ሕጻናት እንኳን ከወላጆቻቸው ኃጢአት የተነሣ በሚመጡ በሽታዎች ይሰቃያሉ። {1MCP 143.1} 1MCPAmh 116.5
ሙሴ፣ የመጀመሪያው ታሪክ ፀሐፊ፣ በዓለም ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ውስጥ ስለ ማህበራዊና ስለ ግለሰብ ሕይወት ግልጽ ዘገባ ይሰጣል፣ ነገር ግን ማየት የተሳነው፣ መስማት የተሳነው፣ ሽባ፣ ወይም ደደብ ሆኖ ስለተወለደ ህጻን ልጅ ምንም ዘገባ አናገኝም። በአራስነት፣ በልጅነት ወይም በወጣትነት ዕድሜ ስለደረሰ የተፈጥሮ ሞት ተመዝግቦ የተቀመጣ አጋጣሚ የለም።…ልጅ ከአባቱ ቀድሞ መሞት ያልተለመደ ስለነበር የዚህን ዓይነት ክስተት መመዝገብ ተገቢ እንደሆነ ተደርጎ ይታይ ነበር፡- ‹‹ሃራን ከአባቱ ከቴራህ ቀድሞ ሞተ።›› ከጥቂቶች በስተቀር ከአዳም ጀምሮ እስከ ኖህ ድረስ የነበሩ አባቶች ወደ አንድ ሺህ ዓመት የቀረበ ዕድሜ ኖረዋል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ የሰው አማካይ ዕድሜ ያለማቋረጥ በመቀነስ ላይ ይገኛል። {1MCP 143.2} 1MCPAmh 116.6
በክርስቶስ የመጀመሪያው ምጻት ጊዜ የሰው ዘር እጅግ ከመበላሸቱ (ከማሽቆልቆሉ) የተነሣ ሽማግሌዎችን ብቻ ሳይሆን በመካከለኛ ዕድሜ የነበሩትንና ልጆችንም ከበሽታቸው እንዲፈወሱ ከየከተማው ወደ አዳኙ ያመጡአቸው ነበር።--CTBH 7, 8, 1890. (CD 117, 118.) {1MCP 143.3} 1MCPAmh 117.1
ልጆች የወላጆቻቸውን የተሳሳቱ ልምዶች መተው አለባቸው።--የጤና ሕጎችን ችላ በማለት ለበሽታ መንገድ ተዘጋጅቶለታል፣ ግብዣም ተደርጎለታል። ብዙዎች ከወላጆቻቸው መተላለፍ የተነሣ ይሰቃያሉ። ወላጆቻቸው ላደረጉት ነገር ተጠያቂ ባይሆኑም የትኞቹ የጤና ሕግን መተላለፍ እንደሆኑና የትኞቹ ደግም እንዳልሆኑ ማረጋገጥ የእነርሱ ተግባር ነው። የወላጆቻቸውን የስህተት ልምዶች መተውና ትክክለኛ በሆነ ኑሮ ራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ ማስቀመጥ አለባቸው። --MH 234 (1905). 144{1MCP 143.4} 1MCPAmh 117.2
የቀደመው ትውልድ ኃጢአቶች ዓለምን በበሽታ እየሞሉ ናቸው።-- ቅድመ አያቶቻችን ዓለምን በበሽታ እየሞሉ ያሉ ወጎችንና የምግብ ፍላጎቶችን አውርሰውናል። በተዛባ የምግብ ፍላጎት አማካይነት፣ የወላጆች ኃጢአቶች፣ አስፈሪ በሆነ ኃይል በልጆች ላይ እስከ ሶስተኛውና እስከ አራተኛው ትውልድ ድረስ ፍርድ አምጥተዋል። የብዙ ትውልዶች መጥፎ አመጋገብ፣ በሕዝብ መካከል እየታዩ ያሉ ስግብግብና ራስን የማስደሰት ልምዶች ምስኪን ቤቶቻችንን፣ ወህኒ ቤቶቻችንን እና የአእምሮ ሕመምተኞች መጠበቂያ ቦታዎቻችንን እየሞሉ ናቸው። ሻይንና ቡናን፣ ወይንን፣ ቢራን፣ እና ሌሎች አስካሪ መጠጦችን በመጠጣት ራስን አለመግዛትና ትምባሆን፣ ኦፒየምንና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን መጠቀም ታላቅ የአእምሮና የአካል ብልሽትን ያስከተለ ሲሆን ይህ ብልሽት ከጊዜ ወደ ጊዜ ያለማቋረጥ እየጨመረ ይገኛል።--RH, July 29, 1884. (CH 49.) {1MCP 144.1} 1MCPAmh 117.3
በውርስ የመጣ የአነቃቂዎች ፍላጎቶት።--ለአንዳንድ ግለሰቦች በቤት ውስጥ ወይንን ወይም አልኮልነት ያለውን የፍራፍሬ ጭማቂ መጠቀም በምንም መንገድ ከጉዳት ነጻ አይደለም። እንዲጠቀሙአቸው ሰይጣን ያለማቋረጥ እያባበላቸው ያለውን የአነቃቂዎችን ፍላጎት ወርሰዋል። ለፈተናዎቹ ከተሸነፉ ማቆም አይችሉም፤ ለእነዚህ ነገሮች ያለው ፍላጎት የማያቋርጥ ጥያቄ ስለሚያስነሳ እስኪያጠፋቸው ድረስ ፍላጎታቸውን ያሟላሉ። አእምሮ ይደነዝዛል ይጨልማልም፤ የማሰብ ችሎታ ልጓሞች ሥራቸውን ያቆሙና በፍትወት አንገት ላይ ይቀመጣሉ።--5T 356, 357 (1885). {1MCP 144.2} 1MCPAmh 117.4
የትንባሆ ክፋት ወደ ልጆች ይተላለፋል።--በልጆችና በወጣቶች መካከል ትንባሆን መጠቀም ሊነገር የማይችል ጉዳት እያስከተለ ነው። ያለፈው ትውልድ ጤናማ ያልሆኑ ልምምዶች በዛሬ ልጆችና ወጣቶች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ። የአእምሮ አቅም ማነስ፣ የአካል ድክመት፣ የተዘበራረቁ ነርቮች እና ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ መስገብገቦች እንደ ቅርስ ከወላጆች ወደ ልጆች ተላልፈዋል። እነዚህ ልምምዶች በልጆች ከመቀጠላቸው የተነሣ ክፉ ውጤቶች እየቀጠሉና እየጨመሩ ናቸው። ለዚህ ሽብር እየፈጠረ ላለው የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ብልሽት የእነዚህ ነገሮች አስተዋጽዖ የሚናቅ አይደለም። --MH 328, 329 (1905). {1MCP 144.3} 1MCPAmh 118.1
ልጆች ዝንባሌን ይወርሳሉ።--ልጆች የስህተት ዝንባሌዎችን ይወርሳሉ፣ ነገር ግን ብዙ ደስ የሚሉ ባሕርያትም አሏቸው። የክፉ ዝንባሌዎች በጥንቃቄ ሲጠበቁና ታምቀው ሲቀሩ መልካም ባሕርያት ደግሞ መጠንከርና ማደግ አለባቸው። ልጆች ያልሆኑትን እንደሆኑ አድርጎ መንገር ለእነርሱ መርዝ ስለሆነ መነገር የለበትም፤ ነገር ግን ወላጆች የተቀደሰ፣ ገርነት ያለበት አክብሮት ሊሰጡአቸው ይገባል፣ ይህን በማድረጋቸው የእነርሱን አመኔታና ፍቅር ያተርፋሉ።--RH, Jan 24, 1907. {1MCP 144.4} 1MCPAmh 118.2
ተገቢ የሆኑ የሙገሳ ቃላት።--እናት ስለ ልጆቿ መልካም ባሕርይ የሙገሳ ቃል መናገር በምትችልበት ጊዜ ሁሉ መናገር አለባት። ለፈጸሙት መልካም ተግባር ማረጋገጫ በሚሰጡ ቃላትና የፍቅር እይታ ማደፋፈር አለባት። ይህ ለልጅ ልብ እንደ ፀሐይ ብርሃን ስለሚሆን ራሱን ወደ ማክበርና በባሕርዩ ወደ መኩራት ይመራል።--3T 532 (1889). {1MCP 145.1} 1MCPAmh 118.3
አንዳንድ ጊዜ ግልፍተኝነት ይወረሳል።--አንዳንዶች ከወላጆቻቸው የተላለፈባቸው ግልፍተኝነት ያላቸው ሲሆን፣ በልጅነት የተማሩት ትምህርት ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ አላስተማራቸውም። ከዚህ እንደ እሳት ከሚነድ ቁጣ ጋር ብዙ ጊዜ ቅናትና ምቀኝነት አንድነት ይፈጥራሉ።--2T 74 (1868). {1MCP 145.2} 1MCPAmh 118.4
ሰይጣን የተወረሱ ድክመቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ ይጠቀማል።--የወደቀው ተፈጥሮአችን የሚያነሳቸውን የማያቋርጡ ጥያቄዎች በራሳችን ብርታት መመለስ አንችልም። በዚህ መስመር ሰይጣን ፈተና ያመጣብናል። ጠላት በውርስ የመጡ ድክመቶችን እንደ መልካም ዕድል ለመጠቀምና በውሸት ማባባያዎቹ በእግዚአብሔር የማይታመኑትን ሊያጠምድ ወደ እያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር እንደሚመጣ ክርስቶስ ያውቅ ነበር። ጌታችን ሰው መራመድ በነበረበት መሬት ላይ በማለፍ ለእኛ የምናሸንፍበትን መንገድ አዘጋጅቷል። ከሰይጣን ጋር በሚደረግ ግጭት ተጎጂዎች በምንሆንበት ቦታ እንድንሆን የእርሱ ፈቃድ አይደለም።…እንዲህ ይላል፡- ‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ›› (ዮሐንስ 16፡ 33)።--DA 122, 123 (1898). {1MCP 145.3} 1MCPAmh 118.5
መለወጥ የተወረሱ ዝንባሌዎችን ይለውጣል።--ትክክለኛ የሆነ መለወጥ ስህተትን ለማድረግ በውርስ የተገኙትንም ሆነ ያሳደግናቸውን ዝንባሌዎች ይለውጣል። የእግዚአብሔር ኃይማኖት ሊቆጠሩ ከማይችሉ ድርና ማጎች በብልጠትና በብልሃት ተጠልፎ የተሰራ ጠንካራ ሸማ ነው። ይህን ሸማ ሙሉ ሊያደርግ የሚችለው ከእግዚአብሔር የሚመጣ ጥበብ ብቻ ነው። በመጀመሪያ ሲታይ ጥሩ መስለው የሚታዩ እጅግ ብዙ ልብሶች አሉ፣ ነገር ግን ፈተናውን ማለፍ አይችሉም። ይደበዝዛሉ። ቀለማቸው ይለቃል። በበጋ ፀሐይ ይደበዝዙና ይጠፋሉ። ልብሶቹ ጥሩ ያልሆነ አያያዝን መቋቋም አይችሉም።--Lt 105, 1893. (6BC 1101.) {1MCP 145.4} 1MCPAmh 119.1
የውርስ ባሪያዎች እንዳንሆን።--ልናስብበት የሚገባው ጥያቄ ‹‹የክርስቶስ ባሕርያት አሉን ወይ? የሚለው ነው። የምንሰጣቸው ሰበቦች ዋጋ ቢስ ናቸው። ሁኔታዎች ሁሉ፣ የምግብ ፍላጎቶቻችንና ሌሎች ፍላጎቶች እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰው ባሪያዎች እንጂ ገዦች መሆን የለባቸውም። ክርስቲያን ለማንኛውም በውርስ ለመጡት ወይም እራሱ ላዳበራቸው ልምዶች ወይም ዝንባሌ ባሪያ መሆን የለበትም።--SpT Series A, No. 9, p 56, 1897. (TM 421.) {1MCP 146.1} 1MCPAmh 119.2
እነዚህን ዝንባሌዎች እንድንዋጋ መላእክት ይረዳሉ።--መላእክት እጅግ በሚፈለጉበት ቦታ ሁል ጊዜ ይገኛሉ። የሚዋጉት እጅግ ጠንካራ ጦርነት ካለባቸው ጋር፣ የውርስ ዝንባሌዎችንና አዝማሚያዎችን መዋጋት ካለባቸው ጋር፣ የቤታቸው ዙሪያ እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ከሆነባቸው ጋር አብረው አሉ።--RH, Apr 16, 1895. (ML 303.) {1MCP 146.2} 1MCPAmh 119.3
እምነት በውርስ የመጡ ጉድለቶችን ያነጻል።--ለቅዱሳት መጻሕፍት ባላቸው ምሁራዊ በሆነ መረዳት መስቀልን በትክክል የሚመለከቱ፣ በኢየሱስ በእውነት የሚያምኑ ሰዎች ለእምነታቸው እርግጠኛ የሆነ መሰረት አላቸው። በፍቅር የሚሰራና ነፍስን በውርስ ከመጡትና በልምድ ካደጉት ጉድለቶች የሚያነፃ ያ እምነት አላቸው።--6T 238 (1900). {1MCP 146.3} 1MCPAmh 119.4
አካባቢ የሚያመጣቸው አስገራሚ ተፅኖዎች።--ሰይጣናዊ ጥንቆላ ባለበት ከባቢ አየር ውስጥ እንኖራለን። በክርስቶስ ፀጋ ባልታጠረ በእያንዳንዱ ነፍስ ዙሪያ ጠላት የፍትወተኛነትን ድግምት ይሸምናል። ፈተናዎች ይመጣሉ፤ ነገር ግን ጠላትን ነቅተን ከጠበቅንና ራስን የመቆጣጠርንና የንጽህናን ሚዛን ከጠበቅን አታላይ መናፍስት በእኛ ላይ ተጽእኖ አይኖራቸውም። ፈተናን ለማደፋፈር አንድም ነገር የማያደርጉ ሰዎች ፈተና በመጣ ጊዜ መቋቋም የሚችሉበት ብርታት ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን ራሳቸውን በክፉው ከባቢ አየር ሥር የሚጠብቁ ሰዎች ቢሸነፉና ከጽናታቸው ቢወድቁ ማንንም ሳይሆን ራሳቸውን እንደ ጥፋተኛ ቆጥረው መውቀስ አለባቸው። ወደፊት አታላይ መናፍስትን በተመለከተ ስለተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች ጥሩ የሆኑ ምክንያቶች ይታያሉ። በዚያን ጊዜ ‹‹በሰማይ ያለው አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ደግሞ ፍጹማን ሁኑ›› የሚሉት የክርስቶስ ቃላት ኃይል ይታያል። ማቴዎስ 5፡ 48። --CT 257 (1913). {1MCP 146.4} 1MCPAmh 120.1
ክፉ አካባቢ የሎጥን ሴት ልጆች አበላሸ።--ሎጥ በዞዓር የኖረው ለአጭር ጊዜ ነበር። ልክ እንደ ሶዶም እዚያም ኃጢአት ስለበዛ ከተማዋ ልትጠፋ ስለምትችል እዚያ ለመኖር ፈራ። ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር እንደተናገረው ዞዓርም በእሳት ተቃጠለች። ሎጥ ቤተሰቡን በዚያች ክፉ ከተማ ተጽእኖ ሥር እንዲሆኑ የደፈረበትን ነገር ሁሉ ተነጥቆ ወደ ተራራ በመሸሽ በዋሻ ውስጥ መኖር ጀመረ። ነገር ግን የሶዶም እርግማን ወደዚህም ተከተለው። የሴት ልጆቹ ኃጢአተኛ ባሕርይ የዚያ መጥፎ ቦታ ክፉ ግንኙነቶች ውጤት ነበር። የዚያ ቦታ የግብረገብ ብልሽት ከባሕርያቸው ጋር እጅግ ስለተጠላለፈ በመልካምና በክፉ መካከል መለየት አቃታቸው። የሎጥ ብቸኛ ዝሪያ የሆኑት ሞአባውያንና አሞናውያን መጥፎ፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ በእግዚአብሔር ላይ ያመጹና የሕዝቡ መራር ጠላቶች ነበሩ። --PP 167, 168 (1890). {1MCP 147.1} 1MCPAmh 120.2
ክፉ ግንኙነቶችን (ሕብረቶችን) ሽሹ።--በተቻለ መጠን ከኃይማኖታዊ ሕይወት ጋር የማይስማሙ ግንኙነቶችን ሁሉ የመሸሽን ጥቅም የሚያስተውሉት ጥቂቶች ናቸው። አከባቢያቸውን በሚመርጡበት ጊዜ ስለ መንፈሳዊ ብልጽግናቸው የመጀመሪያ ቦታ በመስጠት በጥንቃቄ የሚያስቡበት ጥቂቶች ናቸው። {1MCP 147.2} 1MCPAmh 120.3
ወላጆች ከገጠር ይልቅ በከተማ ውስጥ ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በቀላሉ እንደሚያገኙ በማሰብ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ ከተሞች ይተማሉ። ልጆች በትምህርት ቤት በማይሆኑበት ጊዜ የሚሰሩት ነገር ስለማይኖራቸው የጎዳና ትምህርትን ይማራሉ። ከክፉ ግንኙነቶች መጥፎና ከንቱ ሕይወት የመምራትን ልምዶች ያገኛሉ። ወላጆች ይህን ሁሉ ያያሉ፤ ነገር ግን ስህተታቸውን ለማረም መስዋዕትነትን ስለሚጠይቅ ሰይጣን ልጆቻቸውን ሙሉ በሙሉ እስኪቆጣጠር ድረስ እዚያው ይኖራሉ። በእናንተ ጥንቃቄ ሥር እንዲሆኑ የተሰጡአችሁን የከበሩ ነፍሳት አደጋ ላይ ከመጣል ይልቅ እያንዳንዱን ዓላማዊ ጥቅም መስዋዕት ማድረግ ይሻላል። --5T 232 (1882). {1MCP 147.3} 1MCPAmh 120.4
በሰማይ ከባቢ አየር ውስጥ ኑሩ። በጋራ ግንዛቤ እውነተኛ የስነ-መለኮት ትምህርት መመራት አለብን። ነፍሶቻችን በሰማይ ከባቢ አየር መከበብ አለባቸው። ወንዶችና ሴቶች ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው፤ እነርሱ ስላላቸው መልካም ነገር ክፉ እንዲናገሩ የሚያደርግ አንድም ቃል ወይም ተግባር ሳይፈቅዱ ሁል ጊዜ ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው። የክርስቶስ ተከታይ ነኝ የሚል ሰው ራሱን በሀሳብ፣ በቃልና በተግባር ንጹህና ያልተበከለ አድርጎ በመጠበቅ ነቅቶ መጠበቅ አለበት። በሌሎች ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍ የሚያደርግ መሆን አለበት። ሕይወቱ የጽድቅ ፀሐይን ብሩህ ጮራዎች ማንጸባረቅ አለበት።--CT 257, 258 (1913). {1MCP 148.1} 1MCPAmh 121.1
የልጅነት መድሎ መዳረሻን ይወስናል።--ልጆች በትንሽነት ዕድሜያቸው ቅስም ለሚሰብሩ (በራስ መተማመንን ለሚያሳጡ) ተጽእኖዎች ይጋለጣሉ፣ ነገር ግን ክርስቲያን ነን ባይ ወላጆች ራሳቸው እየተከተሉ ያሉበትን የአስተዳደር መንገድ ክፋት መለየት የሚችሉ አይመስሉም። ልጅ በትንሽነት ዕድሜው የተፈጸመበት ተጽእኖ (መድሎ) ባሕርይ የመሆን ዝንባሌን እንደሚያመጣና የግለሰቡን መዳረሻ ለዘላለም ሕይወት ወይም ለዘላለም ሞት እንደሚያዘጋጅ ምነው መገንዘብ በቻሉ! ልጆች ለግብረገብም ሆነ ለመንፈሳዊ ተጽእኖ ተጋላጭ ስለሆኑ በልጅነታቸው በጥበብ የሰለጠኑ ልጆች አንዳንድ ጊዜ ቢሳሳቱም እስከሚጠፉ ድረስ ርቀው አይሄዱም። --ST, Apr 16, 1896. (CG 198.) {1MCP 148.2} 1MCPAmh 121.2
ወላጆች በከፍተኛ ደረጃ ኃላፊነት አለባቸው።--ወላጆች የልጆቻቸውን ባሕርይ ለመቅረጽ በከፍተኛ ደረጃ ኃላፊነት አለባቸው። በተመጣጠነ ቅርጽና ሚዛናዊነት ለይ ማተኮር አለባቸው። ዛሬ ጥቂት ሚዛናዊ የሆኑ አእምሮዎች ያሉበት ምክንያት ወላጆች ደካማ ባሕርያትን የማነቃቃትና ስህተት የሆኑትን የመጨቆን ተግባራቸውን በክፋት ችላ ስላሉ ነው። የእያንዳንዱን ልጅ ዝንባሌዎች ነቅቶ የመጠበቅ እጅግ የከበረ ግዴታ እንዳለባቸው፣ ልጆቻቸው ትክክለኛ የሆኑ ልምዶችና ትክክለኛ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ማሳልጠን ተግባራቸው እንደሆነ አያስታውሱም። --5T 319 (1885). 149 {1MCP 148.3} 1MCPAmh 121.3
በሕጻንነት ጊዜ ጀምሩ።--ልጅ ትክክለኛ የሆነ የባሕርይ አሻራ እንዲወስድ ወላጆች በልጃቸው ላይ የሚሰሩት ሥራ መጀመር ያለበት በሕጻንነት ጊዜ ነው፤ ይህ ካልሆነ ዓለም በልጁ አእምሮና ልብ ላይ የራሱን ማህተም ያሳርፍበታል። --RH, Aug 30, 1881.(CG 193.) {1MCP 149.1} 1MCPAmh 121.4
የመጀመሪያ ሶስት ዓመታት አስፈላጊነት (ጠቃሚነት)።--እናቶች ሆይ፣ ልጆችን በሕይወታቸው የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ በደንብ ሥነ-ሥርዓትን ማስተማራችሁን እርግጠኞች ሁኑ። የራሳቸውን ምኞትና ፍላጎት እንዲመሰርቱ አትፍቀዱላቸው። እናት ለልጇ አእምሮ መሆን አለባት። የመጀመሪያዎቹ ሶስት አመታት ትንሹን ችግኝ የማቃናት ዓመታት ናቸው። እናቶች የዚህን ጊዜ አስፈላጊነት መረዳት አለባቸው። ያ መሰረት የሚጣልበት ጊዜ ነው። --MS 64, 1899. (CG 194.) {1MCP 149.2} 1MCPAmh 122.1
ባሕርይን መመስረትን በተመለከተ የመጀመሪያዎቹ ሰባት ዓመታት ብዙ ድርሻ አላቸው።--ልጆችን በልጅነት ዕድሜያቸው በማሰልጠን አስፈላጊነት ላይ የሚሰጠው ትኩረት እጅግ ብዙ አይደለም። የልጅን ባሕርይ ምስረታ በተመለከተ ልጁ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ዓመታት ውስጥ የሚማራቸው ትምህርቶች ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ሁሉ ከሚማራቸው ትምህርቶች የበለጠ ጠቀሜታ አላቸው። --MS 2, 1903. (CG 193.) {1MCP 149.3} 1MCPAmh 122.2
የመጀመሪያዎቹ ትምህርቶች አይረሱም።--ሕጻናትም ሆኑ ልጆች ወይም ወጣቶች ከአባት፣ ከእናት ወይም ከማንኛውም የቤተ ሰብ አባል ትዕግስት የጎደለውን ቃል መስማት የለባቸውም፤ ልጆች የባሕርይ አሻራን የሚቀበሉት በልጅነት ዕድሜያቸው ስለሆነ ዛሬ ወላጆች እንዲሆኑ ያደረጉአቸውን ነገር ነገ፣ በቀጣዩ ቀንና ቀጥሎ ባሉት ቀናት ይሆናሉ። በልጅ አእምሮ የተቀረጹ የመጀመሪያዎቹ ትምህርቶች በፍጹም አይረሱም።… {1MCP 149.4} 1MCPAmh 122.3
በልባቸው ውስጥ በጣም በትንሽነታቸው ያረፉ አሻራዎች ቀጥለው ባሉት አመታት ውስጥ ይታያሉ። ሊቀበሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይጠፉም። --MS 57, 1897. (CG 193, 194.) {1MCP 149.5} 1MCPAmh 122.4
የልጅነት የአካል እድገት።--በልጅ ሕይወት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወይም ሰባት ዓመታት ከአእምሮ እውቀት ስልጠና ይልቅ ለአካላዊ ሥልጠና የተለየ ትኩረት መሰጠት አለበት። ከዚህ ጊዜ በኋላ፣ የአካል አቋሙ ጥሩ ከሆነ፣ የሁለቱም ትምህርት ትኩረት ማግኘት አለበት። የሕጻንነት ዕድሜ እስከ ስድስት ወይም ሰባት ዓመት ይደርሳል። በዚህን ወቅት ልጆች እንደ ትንሽ ጠቦቶች በቤት ዙሪያና በጊቢ ውስጥ እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ፣ መንፈሳቸው ደስ እንዳለው፣ ያለ አንዳች ጭንቀትና ችግር እንዲዘሉ መተው አለባቸው። {1MCP 149.6} 1MCPAmh 122.5
እንደ እነዚህ ላሉ አእምሮዎች ብቸኛ መምህራን ወላጆች፣ በተለይም እናቶች መሆን አለባቸው። ከመጻሕፍት ማስተማር የለባቸውም። ልጆች በአጠቃላይ የተፈጥሮ ነገሮችን ለመማር ይጠይቃሉ። ስለሚያዩአቸውና ስለሚሰሙአቸው ነገሮች ጥያቄዎችን ስለሚጠይቁ እነዚህን አጋጣሚዎች ለማስተማር መጠቀምና እነዚህን ትናንሽ ጥያቄዎች በትዕግስት መመለስ አለባቸው። በዚህ ሁኔታ ጠላት ከሚያገኘው የተሻለ ዕድል ስለሚያገኙ በልባቸው ጥሩ ዘር በመዝራት፣ ክፉው ሥር እንዲሰድ ቦታ ባለመስጠት፣ የልጆቻቸውን አእምሮ ከጥቃት መከላከል አለባቸው። በልጆች ባሕርይ ግንባታ ውስጥ የሚፈለገው ነገር በለጋነት ዕድሜ እናት በፍቅር የምትሰጣቸው ትምህርቶች ናቸው። --HL (Part 2) 44. (2SM 437.) {1MCP 150.1} 1MCPAmh 123.1
ለመጀመሪያ ልጅ የተለየ ጥንቃቄ።--የመጀመሪያ ልጅ ቀጥለው የሚወለዱትን ስለሚያሰለጥን በተለየ ሁኔታ በትልቅ ጥንቃቄ መሰልጠን አለበት። ልጆች የሚያድጉት በዙሪያቸው ያሉት የሚያሳድሩባቸውን ተጽእኖ በመቀበል ነው። የሚይዙአቸው ሰዎች የሚጮሁና ትዕግስት የለሾች ከሆኑ ልጆቹም ጯሂዎችና ትዕግስት የለሾች ይሆናሉ። --MS 64, 1899. (CG 27.) {1MCP 150.2} 1MCPAmh 123.2
ልዩነት ላላቸው ልጆች የተለያየ አከባቢ።--ከሌሎች ልጆች ይልቅ ብዙ ትዕግስት ያለበት ሥርዓት የማስያዝና በትህትና የማሰልጠን ሥራ የሚያስፈልጋቸው አንዳንድ ልጆች አሉ። ተስፋ የማይሰጡ ባሕርያትን እንደ ቅርስ ስለተቀበሉ የበለጠ ርኅራኄና ፍቅር ያስፈልጋቸዋል። ዓላማን ለማሳካት ተግቶ በመስራት እነዚህ መንገድ የሳቱ ልጆች በጌታ ሥራ ውስጥ ላለው ቦታ ሊዘጋጁ ይችላሉ። ቢቀሰቀሱ ኖሮ ብዙ ከሚጠበቅባቸው ሰዎች ቀድመው ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችሉአቸው ያልዳበሩ ኃይሎች ሊኖሩአቸው ይችላሉ።--CT 115, 116 (1913). {1MCP 150.3} 1MCPAmh 123.3
ልምዶች በዕድሜ ቆይታ አይለወጡም።… ልጅ የሚያያቸውና የሚሰማቸው ነገሮች ኋላ በሕይወት ውስጥ የሚከሰቱ ማናቸውም ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ሊፍቁአቸው የማይችሉአቸውን ጥልቅ የሆኑ መስመሮች ለጋ በሆነ አእምሮ ውስጥ እያሰመሩ ናቸው። አሁን አእምሮ መልክ እየያዘና የፍቅር ስሜቶች አቅጣጫና ብርታት እያገኙ ናቸው። በአንድ መስመር የሚደጋገሙ ድርጊቶች ልምድ ይሆናሉ። እነዚህ ነገሮች በኋለኛው ሕይወት ጽኑ በሆነ ስልጠና ሊስተካከሉ ይችሉ ይሆናል፣ ነገር ግን ሊለወጡ አይችሉም። --GH, Jan, 1880. (CG 199, 200.) {1MCP 150.4} 1MCPAmh 123.4
የደግነት ፈዋሽ ተጽእኖ።--በየዋህነት፣ በደግነት፣ እና በጭምትነት ተጽእኖ ሥር የሚያጠፋ ሳይሆን የሚፈውስ ከባቢ አየር ይፈጠራል።--Lt 320, 1906. (ML 152.) {1MCP 151.1} 1MCPAmh 124.1