Go to full page →

72—ሁለተኛው ሞት EWAmh 218

ሰይጣን ለቁጥር የሚያታክቱ ተከታዮቹን አመለካከት ለማመስ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሲገሰግስ ነገር ግን በዚህን ወቅት ከእግዚአብሔር የተላከ እሳት በታላላቅ ሰዎች፣ በኃያላን፣ በዝነኞች፣ በድኾችና ችጋረኞች ላይ በመውረድ በአንድነት በላቸው:፡፡ አንዳንዶች ወዲያውኑ ሲጠፉ ሌሎች ግን ለተጨማሪ ጊዜያት እንደተሰቃዩ ተመልክቻለሁ፡፡ ኃጥአን በሠሩት መጠን ቅጣት ተቀብለዋል፡፡ እሳቱ ከእነርሱ ላይ በልቶ ያልጨረሰው ክፍል እስካለ ድረስ እየነደደ በመቆየቱ አንዳንዶች ለብዙ ቀናት በሥቃይ ቆይተው ነበር፡፡ መልአኩ እንዲህ አለኝ «ህይወትን የሚበላው ትል አይሞትም፧ እሣቱ የሚበላው በጣም አነስተኛ ክፍል እንኳ እስካለ ድረስ አይጠፋም»፡፡: EWAmh 218.1

ሰይጣንና መላእክቱ ከእግዚአብሔር በወረደው እሳት ለረጅም ጊዜ ተሰቃይተዋል፡፡ ሰይጣን ቅጣት የተቀፀለው ለራሱ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የዳትን ቅዱሳን ቅጣት ጭምር ነበር የወሰደው፡፡ ምክንያቱም የእነዚህ ህዝቦች ኃጢአት ወደ እርሱ ተላልፎ ነበር፡፡ በተጨማሪ ሰይጣን ያሳታቸውን ነፍሳት ቅጣት መቀበል ነበረበት፡፡ ከዚያም ሰይጣንና ሰራዊቱ ከመላው ኃጥአን ጋር እሳት እንደበላቸውና አምላካዊው ፍትሕ እንደተሟላ ተመለከትኩ፡፡ በዚህን ጊዜ መላው የመላእክት ሰራዊትና የተዋጁት ቅዱሳን ድምፆቻቸውን ከፍ ድርገው «አሜን!” አሉ፡፡ EWAmh 218.2

መልአኩ እንዲህ አለኝ «ሰይጣን ሥር ሲሆን ልጆቹ ደግሞ ቅርንጫፎች ናቸው፡፡ እነርሱ አሁን እሳት እየበላቸው ያለ ሥርና ቅርንጫፎች ናቸው፡፡ ዘላለማዊውን ሞት ሞተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ትንሳኤ አይኖራቸውም፡፡ እግዚአብሔርም ንጹህ ዩኒቨርስ ይኖረዋል” ከዚህ በኋላ ኃጢአትን የበላውንና ምድርን ያጠራውን እሳት ተመለከትኩ፡፡ እንደገና ምድር ነጽታ አየሁ፡፡ አንዳችም የእርግማን ምልክት አልነበረም፡፡ የተሰባበረና ጎርባጣ የነበረው ምድር አሁን ግን ደልዳላና ሰፊ መስክ ሆኖ አየሁት፡፡ መላው ዩኒቨርስ ከኃጢአት ጸድ ቶና ታላቁ ተጋድሎ ለዘላለም አክትሞ ነበር ወደ የትኛውም በኩል ስንመለከት ዐይኖቻችን የሚያርፉባቸው ነገሮች ሁሉ ውብና ቅዱስ ነበሩ የዳኑት በሙሉ አብረቅራቂ አክሊሎቻቸውን በአዳኛቸው የሱስ እግሮች ስር በማኖርና በፍቅር በፊቱ በመነጠፍ ከዘላለም እስከ ዘላለም ህያው ለሆነው ለእርሱ ሰገዱለት፡፡ ውብ የሆነችውን አዲሲቱን ምድር ቅዱሳን ከነሙሉ ክብሯ በመውረስ ዘላለማዊ መኖሪያቸው ሆነች: በዚህን ጊዜ ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑሉ ህዝብ ለቅዱሳን ተሰጠ፡፡ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ይሆናል፡፡ EWAmh 219.1