Go to full page →

ሽማግሌው ቡትለር እጅግ በጣም ጠቃሚ ሰራተኛ Amh2SM 226

ሽማግሌ ጂ አይ ቡትለርን እንደገና በሥራ ላይ የምንመለከተው በእርካታና ለእግዚአብሔር ምሥጋና በማቅረብ ስሜቶች ነው፡፡ የሸበቱ ጸጉሮች መከራ ምን እንደሆነ እንደሚገነዘብ ይመሰክራሉ፡፡ ወደ እኛ ሥራ በድጋሚ እንኳን ደህና መጣህ እያልን እጅግ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ሰራተኞቻችን እንደ አንዱ አድርገን እንቆጥረዋለን፡፡ መልእክቱ በተላለፈባቸው ቀደምት ጊዜያቶች ምስክርነታቸውን የተሸከሙትን ወንድሞች የአካል፣ የአእምሮና የመንፈስ ኃይሎችን በመጠበቅ ረገድ ጠቢባን እንዲሆኑ ጌታ ይርዳቸው፡፡ እግዚአብሔር የማገናዘብ ኃይል እንዲሰጣችሁ እና በአካል ጤና ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ሕጎችን እንድታስተውሉና ለመታዘዝ ቁርጥ ውሳኔ እንድታደርጉ እርሱ እንደሚሻ እንድነግራችሁ በጌታ ታዝዣለሁ፡፡ እነዚህ ሕጎች የእግዚአብሔር ሕጎች ናቸው፡፡ ሕዝብ የአካል፣ የአእምሮና የመንፈስ ማሽቆልቆልን በሚያስከትል ብርቱ የሆነ የክፋት ማዕበል ተጠራርጎ እንዳይወሰድ በማድረግ ረገድ እያንዳንዱ ፈር ቀዳጅ ድርሻውን ለመወጣት በዕጣውና በቦታው እንዲቆም እግዚአብሔር ይሻል፡፡ ወንድሞቼ ሆይ፣ ጦርነቱ እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ የጦር መሣሪያችሁን እንዳታወልቁ እግዚአብሔር ይሻል፡፡ ሞኞች አትሁኑ፤ ከመጠን በላይ አትስሩ፡፡ የእረፍት ጊዜ ይኑራችሁ፡፡ Amh2SM 226.1

በጦርነት ላይ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ድል የነሳች ቤተ ክርስቲያን አይደለችም፡፡ የተፈተኑ አገልጋዮቹ፣ በሕይወት እስካሉ ድረስ መሻትን የመግዛት ተሃድሶን እንዲከተሉ ጌታ ይሻል፡፡ መሻትን የመግዛት ባንዲራን አውለብልቡ፡፡ ሰዎች በሁሉም ነገር ውስጥ ጥብቅ የሆነ መሻትን መግዛትን እንዲለማመዱና የአካል ሕጎችን በመታዘዝ አሸናፊዎች እንዲሆኑ አስተምሯቸው፡፡ ለእግዚአብሔር እውነት ጸንታችሁ ቁሙ፡፡ በሕዝብ ፊት፣ «የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው» (ራዕይ 14፡ 12) የሚል ጽሁፍ ያለበትን አርማ ከፍ አድርጉ፡፡… Amh2SM 226.2