Go to full page →

ወጣቶች ልምድ ካላቸው ሠራተኞች ጋር መተባበር አለባቸው Amh2SM 229

በዕድሜ የገፉ ሰዎች ሁሉንም ሀላፊነቶች፣ ሁሉንም ሸክሞች መሸከም እንዳለባቸው ማሰብ የለባቸውም፡፡ በፊታችን ያለማቋረጥ አዳዲስ የስራ መስኮች እየተከፈቱ ናቸው፡፡ ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን ከሚያስተውሉ፣ ለረዥም ጊዜ ቃሉን አድራጊዎች ከነበሩ፣ በየዕለቱ በክርስቶስ ላይ በመደገፍ እውነትን ወደ ተግባራዊ ሕይወት ካመጡ፣ እንደ ዳንኤል ጌታን ከሚሹ፣ ልምድ ካላቸው ሠራተኞች ጋር ሕብረት ይፍጠሩ፡፡ ዳንኤል በቀን ሶስት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ልመናውን አቀረበ፡፡ በምክር ብርቱ የሆነው የጥበብና የኃይል ምንጭ መሆኑን አወቀ፡፡ እውነት በክርስቶስ እንዳለ፣ በሁለት ወገን ስለት ያለው የመንፈስ ሰይፍ የጦር መሣሪያው ነበር፡፡ Amh2SM 229.1

በቃል፣ በመንፈስ፣ በመርህ፣ እግዚአብሔርን መታመኛቸው ያደረጉ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ለሚፈጥሩት ወጣቶች ምሳሌ ናቸው፡፡ እነዚህ ታማኝ የእግዚአብሔር ባርያዎች ራሳቸው በክርስቶስ የፍቅር ገመድ ወደ ወጣቶች ስለተሳቡ ወጣቶቹን በፍቅር ገመድ ወደ ራሳቸው በመሳብ ከእነርሱ ጋር መቆራኘት አለባቸው፡፡ The Review and Herald, March 20, 1900. Amh2SM 229.2