Go to full page →

ምዕራፍ 3—የ«ቅዱስ ሥጋ» አስተምህሮ Amh2SM 31

[የኮንፍረንስ ፕሬዝደንትን እና የተለያዩ ሰራተኞችን እጅግ አስከፊ ወደሆነ ስህተት የመራው «የቅዱስ ሥጋ አስተምህሮ» የሚል ስያሜ የተሰጠው የጽንፈኝነት ትምህርት የተጀመረው በ1900 ዓ.ም በኢንዲያና ነበር፡፡ ይህ ንድፈ ሀሳብ አዳኙን የሚከተሉ ሰዎች «በጌተሰማኔ የአትክልት ቦታ» ልምምድ ውስጥ በማለፍ፣ ለመነጠቅ አስፈላጊ የሆነ ዝግጅት እንዲሆን በአካላቸው ኃጢአት የለሽነትን በመቀበል የወደቀው ተፈጥሮአቸው ወደ ፍጽምና ደረጃ መድረስ አለበት ይላል፡፡ የዓይን ምስክሮች መግለጫ እንደዘገበው የጽንፈኞቹ አገልግሎቶች እንደ ኦርጋን፣ ዋሽንት፣ ጥሩምባ፣ ከበሮ፣ ነጋሪት እና የመሳሰሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በመጠቀም በሚያነቃቃ ከፍተኛ ድምጽ የታጀቡ ነበሩ፡፡ በጉባኤው መካከል ያለ ሰው ደክሞና ራሱን ስቶ ከመቀመጫው እስኪወድቅ ድረስ አካላዊ እንቅስቃሴ ይፈልጉ፣ ይጮኹ፣ ይጸልዩና ይዘምሩ ነበር፡፡ ለዚሁ ተግባር በመተላለፊያው ላይ ወደ ላይና ታች ይሄዱ የነበሩ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች የወደቀውን ሰው ወደ መድረክ ይጎትቱታል፡፡ እጅግ ብዙ ሰዎች ሆነው አንዳንዶች እየጸለዩ፣ ሌሎች እየጮኹ ተዘርሮ በወደቀው አካል ዙሪያ ይሰበሰባሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ተራ በተራ ሳይሆን ሁላቸውም በአንድ ጊዜ ነበር፡፡ ግለሰቡ ወደ አእምሮው ሲመለስ በጌተሰማኔ ልምምድ ካለፉት፣ ቅዱስ ሥጋ ከተቀበሉት እና የመነጠቅ እምነት ካላቸው መካከል ይቆጠር ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በፍጹም ኃጢአት እንደማይሰራና እንደማይሞት ይረጋገጥለታል፡፡ ይህንን ጽንፈኝነት እንዲጋፈጡ መሪ ከነበሩ የድርጅታችን አገልጋዮች መካከል ሁለቱ፣ ኤልደር ኤስ. ኤን፣ ሃስከል እና ኤ. ጄ. ብሪድ፣ ከመስከረም 13 እስከ 23 ቀን 1900 ዓ.ም ድረስ በኢንዲያና ግዛት ሙንሲ በተባለ ቦታ ይደረግ ወደነበረው ስብሰባ ተላኩ፡፡ ሚስስ ኋይት ገና በአውስትራሊያ እያለች በጥር ወር 1900 ዓ.ም እነዚህ እድገቶች ታይተዋት ስለነበር ከዚህ በታች ባሉት ሁለት መልእክቶች እንደታየው የማስጠንቀቂያ ምስርነቶችን አስተላልፋ ነበር፡፡ --COMPILERS.] {2SM 31.1} Amh2SM 31.1