Go to full page →

በጌታ የሚሞቱ ሙታን የተባረኩ ናቸው Amh2SM 261

በእናት ሞት ምክንያት የተሰጠ ማጽናኛ Amh2SM 261

ውድ እህት፣

የእናትሽን ሞት በተመለከተ ደብዳቤውን አንብቤያለሁ፣ ልነግርሽ የምችለው “በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁአን ናቸው” (ራዕይ 14፡ 13) የሚለውን ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ እናትሽ በጣም ደክማ ቆይታለች፡፡ ያለመሰልቸት ተጠንቅቀሽላታል፡፡ አሁን ፊቷን ማየት አለመቻልሽ ታላቅ ሀዘን ሊሆንብሽ ይችላል፡፡ አጠገብሽ የምንኖር ቢሆን ኖሮ ተለይና ትንሽ እረፊ እንልሽ ነበር፡፡ ነገር ግን ያሉብሽ ሀላፊነቶች ጊዜሽን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ በጌታ ታመኚ እልሻለሁ፡፡ Amh2SM 261.2

የእናትሽ ሞት በጣም ይሰማሻል፤ ነገር ግን እኔ የማዝነው ለሞቱት ጸድቃን ሳይሆን በሕይወት ላሉት እንደሆነ እነግርሻለሁ፡፡ እናትሽን የቀበርሽው የእግዚአብሔር መለከት ሲነፋ ከመቃብር እንደምትነሳ ሙሉ በሙሉ ተስፋ በማድረግ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡…የምትወጂያቸውን ሰዎች መቅበር ማለት ምን ማለት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ አባቴ፣ እናቴ፣ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ባለቤቴና ከልጆቼ ሁለቱ በመቃብር ተኝተው ይገኛሉ፡፡ በሕይወት ያለነው እህቴ ሜሪ፣ እኔና ሁለቱ ልጆቼ ነን፡፡--Letter 98, 1903. Amh2SM 261.3