Go to full page →

ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እያሳዩ ለሚሄዱ የህክምና ሥርዓቶች የተሰጠ ማረጋገጫ Amh2SM 303

የደም ልገሳ፡፡ አንድ ሕይወትን ያዳነ ነገር አለ፤ እርሱም የአንድን ሰው ደም ለሌላ ሰው መስጠት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ነገር ለአንተ ከባድና ምናልባትም ልታደርገው የማትችለው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲያው መደረግ እንዳለበት ሀሳብ እሰጣለሁ፡፡ Medical Ministry, pp. 286, 287 (To Dr. D. H. Kress). Amh2SM 303.2

ክትባት፡፡ የፈንጣጣ ክትባትን በተመለከተ ከሚስስ ኋይት ጸሐፊዎች መካከል አንዱ የሆነው ዲ ኢ ሮብንሰን ሰኔ 12 ቀን 1931 ዓ.ም ሚስስ ኋይት ስለ ክትባት የነበራትን አመለካከት እንደሚከተለው ጽፎታል፡- Amh2SM 303.3

«ስለ ክትባትና ከሰውነት ውስጥ የሚወሰደውን እዥ ለክትባት መጠቀምን በተመለከተ ቁርጥ ያለና ትክክለኛ መረጃ ትጠይቃለህ፡፡ Amh2SM 303.4

«ለዚህ ጥያቄ በጣም አጠር ያለ መልስ የሚሆነው ተመዝግቦ ያለው ማንኛውም መረጃ እንደሚያሳየው በማንኛቸውም ጽሁፎቿ ውስጥ እነዚህን ነገሮች በተመለከተ የጠቀሰችው ነገር የለም የሚል ነው፡፡ Amh2SM 303.5

«ነገር ግን እሷ ትኖርበት በነበረው አከባቢ የፈንጣጣ ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ ራሷ መከተቧንና ረዳቶቿ፣ ከእሷ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች እንዲከተቡ እንደገፋፋች ለማወቅ ፍላጎት ይኖርሃል፡፡ ሚስስ ኋይት ይህንን እርምጃ ስትወስድ የተገነዘበችው እውነታ ቢኖር ክትባት ሰውነት ፈንጣጣን ሙሉ በሙሉ እንዲቋቋም ወይም ፈንጣጣው ግለሰቡን ከያዘውም የሚያስከትለውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያቀል ነበር፡፡ ይህንን ቅድመ-ጥንቃቄ ካልወሰዱ ሌሎችን ለአደጋ እንደሚያጋልጡም ተገንዝባለች፡፡” ዲ ኢ ሮብንሰን፡፡ Amh2SM 303.6

በሎማሊንዳ የሚሰጠው የጨረር ሕክምና፡፡ በግንባሬ ላይ ለነበረው ጥቁር ነጥብ ለበርካታ ሳምንታት የጨረር ሕክምናን ወስጃለሁ፡፡ ሕክምናውን በአጠቃላይ ለሃያ ሰባት ጊዜ ከወሰድኩ በኋላ ምልክቱ ሙሉ በሙሉ ጠፋልኝ፡፡ ለዚህ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፡፡ Letter 30, 1911 (To her son J. E. White). Amh2SM 303.7