Go to full page →

ለጸሎት ተገቢ ያልሆነ ቦታ የለም Amh2SM 316

ወደ እግዚአብሔር ልመናችንን ለማቅረብ ተገቢ ያልሆነ ቦታና ጊዜ የለም፡፡ …በተጨናነቀ መንገድ ላይም ሆነ በሥራ ቦታችን ወደ እግዚአብሔር ልመናችንን ልናቀርብ እና ነህምያ በንጉሡ አርጤክሰስ ፊት ጥያቄውን ባቀረበ ጊዜ እንዳደረገው ለመለኮታዊ አመራር መለመን እንችላለን፡፡ Steps to Christ (pocket ed.) p. 99. Amh2SM 316.2

በመንገድ ላይ እየሄድን ከኢየሱስ ጋር ልንነጋገር እንችላለን፤ እርሱም በቀኝ እጅህ ነኝ ይለናል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በልባችን ውስጥ ልንነጋገር እንችላለን፤ ከእግዚአብሔር ጋር እንደ ጓደኛ አብረን ልንጓዝ እንችላለን፡፡ በዕለታዊ ሥራችን ስንጠመድ የማንም ሰው ጆሮ ሳይሰማ የልባችንን ምኞት ልንተነፍስ እንችላለን፤ ነገር ግን ያ ቃል ሳይሰማ ሞቶ ወይም ጠፍቶ አይቀርም፡፡ የነፍስን ፍላጎት ምንም ነገር አስምጦ አያስቀርም፡፡ ከመንገድ ዋካታ እና ከማሽን ጩኸት በላይ ይነሳል፡፡ እየተናገርን ያለነው ለእግዚአብሔር ስለሆነ ጸሎታችንን ይሰማል፡፡ Gospel Workers, p. 251. Amh2SM 316.3

ለመጸለይ ሁልጊዜ በጉልበታችሁ መንበርከክ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ብቻችሁን ስትሆኑ፣ ስትራመዱ እና በዕለታዊው ሥራችሁ ተጠምዳችሁ ሳላችሁ ከአዳኝ ጋር የመነጋገርን ልምድ አዳብሩ፡፡ The Ministry of Healing, pp. 510, 511. Amh2SM 316.4