Go to full page →

ገቢ ለሚቀንስበት ቀን መዘጋጀት Amh2SM 329

መቆጠብ እንደሚገባችሁ ቆጥባችሁ ቢሆን ኖሮ ዛሬ በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ለመጠቀምና የእግዚአብሔርን ሥራ ለመርዳት የተጠራቀመ ሃብት ይኖራችሁ ነበር፡፡ በየሳምንቱ ከምታገኙት ክፍያ ውስጥ የተወሰነው መቀመጥና ትክክለኛ የሆነ እጦት እያስቸገራችሁ ካልሆነ በስተቀር፣ ወይም ገንዘቡን ለሰጣችሁ እግዚአብሔር በሥጦታ መልክ ለመመለስ ካልፈለጋችሁ በስተቀር በምንም ምክንያት መነካት የለበትም፡፡ Amh2SM 329.3

አንተ ብትታመምና ከዚህ የተነሳ በገቢህ የሚተዳደር ቤተሰብ ያንን ገቢ ቢነፈግ ኖሮ መጠቀም እንዲችል ያገኘኸው ገቢ በትንሹም ቢሆን እንዲቆጠብ በጥበብ በቁጠባ ወጪ አላደረግክም፡፡ አንተ ገቢ በማይገኝበት ቦታ ብትሆን ቤተሰብህ የሚደገፍበት የሆነ ነገር መኖር አለበት፡፡ Letter 5, 1877. Amh2SM 329.4