Go to full page →

በራስ ፈቃድ የሚደረግ ትርኢት የሀሰት ሥራ ማስረጃ ነው Amh2SM 99

ይህ ወንድምና ባለቤቱ በሐዋርያት ላይ በወረደው ኃይል መንፈስ ቅዱስን ከመቀበላቸው የተነሳ እንደመጣላቸው የሚናገሩትን ልምምዳቸውን ሲዘረዝሩ ሳለ የሚናገሩት ነገር በቀደምት ልምምዳችን ወቅት እንድንጋፈጠውና እንድናርመው የተጠራነው ነገር ትክክለኛ ቅጂ ይመስል ነበር፡፡ {2SM 99.3} Amh2SM 99.3

ወደ ቃለ መጠይቃችን መዝጊያ አከባቢ፣ በጸሎት ውስጥ ሆነን ሳለን እነርሱ እንደገለጹልኝ ሁሉ ባለቤቱ ወደ ልምምዱ ትገባና ያ ልምምዷ ከእግዚአብሔር እንደሆነና እንዳልሆነ እኔ እንድለይ በሚል ሀሳብ ወንድም ኤል በጸሎት አንድ እንድንሆን ሀሳብ አቀረበ፡፡ በዚህ ሀሳብ መስማማት አልቻልኩም ነበር፡፡ ያልተስማማሁበት ምክንያት አንድ ሰው እነዚህን ልዩ የሆኑ መገለጦችን ለማሳየት ሲጠይቅ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ላለመሆኑ ጽኑ ማስረጃ እንደሆነ መመሪያ ተሰጥቶኝ ስለነበር ነው፡፡ --Letter 338, 1908. {2SM 99.4} Amh2SM 99.4