Go to full page →

ማንኛውም እውነተኛ መልእክት ጊዜን አይወስንም Amh2SM 113

ክርስቶስ መቼ እንደሚመጣ ወይም እንደማይመጣ ጊዜ የሚወስን ማንም ሰው እውነተኛ መልእክት የለውም፡፡ ክርስቶስ መምጫውን በአምስት አመት፣ በአስር አመት ወይም በሃያ አመት ያዘገያል ብሎ መልእክት እንዲሰጥ እግዚአብሔር ለማንም ሥልጣን እንደማይሰጥ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ «የሰው ልጅ ባላሰባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ የተዘጋጃችሁ ሁኑ» (ማቴ. 24፡ 44)፡፡ ይህ መልእክታችን ነው፣ ይህ በሰማይ መካከል እየበረሩ ያሉት ሶስቱ መላእክት እያወጁ ያሉት መልእክት ነው፡፡ አሁን መሰራት ያለበት ሥራ ይህን የመጨረሻውን የምህረት መልእክት ለወደቀው ዓለም ማሰማት ነው፡፡ አዲስ ሕይወት ከሰማይ እየመጣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በሙሉ እየተቆጣጠራቸው ነው፡፡ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክፍፍል ይመጣል፡፡ ሁለት ቡድኖች ይፈጠራሉ፡፡ ስንዴና እንክርዳድ ለመከር አብረው ያድጋሉ፡፡ {2SM 113.3} Amh2SM 113.3

ወደ ፍጻሜ እየተቃረብን ስንሄድ ሥራው በጥልቀት እያደገና የበለጠ ቅንነት ያለበት እየሆነ ይሄዳል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው በመስራት ላይ ያሉ በሙሉ አንዴ ለቅዱሳን ለተሰጠው እምነት ከሙሉ ልባቸው በቅንነት ጥብቅና ይቆማሉ፡፡ ከክብሩ የተነሳ ምድርን እያበራ ካለው ከወቅቱ እውነት ማንም ሊመልሳቸው አይችልም፡፡ ከእግዚአብሔር ክብር በስተቀር ጥብቅና ሊቆምለት የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ ጸንቶ መቆም የሚችለው አለት የዘመናት አለት ብቻ ነው፡፡ በዚህ በስህተት በተሞላ ዘመን መጠጊያ መሆን የሚችለው በክርስቶስ ያለው እውነት ነው፡፡. . . {2SM 114.1} Amh2SM 114.1