Go to full page →

ውድ የሆኑ ነገሮችን መለማመድን አስወግዱ Amh2SM 188

ሰራተኞች አርቀው ለመመልከት መንቃት አለባቸው፡፡ በብዙዎች ዘንድ ራስን የመካድና መስዋዕት የማድረግ ልምድ ስለሞተ እነዚህ ነገሮች እንደገና ከሙታን መነሳት አለባቸው፡፡ ሰዎች እንዲከፈላቸው እየጠየቁት ያለው ከፍተኛ ደሞዝ የጌታን ግምጃ ቤት ቀስ በቀስ እያዳከመው መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ከግል ፍላጎቶቻቸው ላይ እያቆራኙ ስለሆነ ተግባሮቻቸው ለዓለም «ጌታዬ ይዘገያል” (ማቴ. 24፡ 48) የሚል መልእክት እያስተላለፈ ነው፡፡ ይህ ነገር መለወጥ የለበትምን? የሰራተኞች አለቃ ወዳስቀመጠው ታላቅ ምሳሌነት መድረስ የሚችል ማን ነው? --Letter 120, 1899. Amh2SM 188.2

አጥጋቢ ስላልሆነው ደሞዛችሁ አትናገሩ፡፡ ውድ ልብሶችን ወይም ቁሳቁሶችን የማግኘትን ፍላጎት አታጎልብቱ፡፡ ሥራው እንደ ጀመረው ቀላል በሆነ ራስን መካድና በእምነት ወደ ፊት ይቀጥል፡፡ የተለየ ሥርዓት ይምጣ፡፡--Letter 94, 1899. Amh2SM 188.3