Go to full page →

አሁን ያለውን ሥርዓት የመለወጥ ፍላጎት Amh2SM 23

የተለየ የመነቃቃት ወቅትን በመጠበቅ ከመኖር ይልቅ ነፍሳት እንዲድኑ መደረግ ያለበትን በማድረግ ዛሬ ያሉንን የተለዩ ዕድሎች ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ማሻሸል አለብን፡፡ እግዚአብሔር በራሱ ኃይል ሥር ስላስቀመጣቸው እና ከሰዎች ስለሰወራቸው ስለ ዘመንና ጊዜ በማሰላሰል የአእምሮ ኃይሎቻችንን ከመጨረስ ይልቅ አሁን ያሉ ተግባራትን ለመፈጸም፣ እውነትን ባለማግኘታቸው እየሞቱ ላሉ ነፍሳት በሰብዓዊ ሀሳብ ያልተበከለውን የሕይወት እንጀራ ለመስጠት ራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር አሳልፈን መስጠት አለብን፡፡. . . {2SM 23.1} Amh2SM 23.1

ከወንጌል ትህትና በላይ የመሆን ቀጣይነት ባለው አደጋ ውስጥ ነን፡፡ ሰዎች በመንፈሳዊ ሁኔታ ከፍ ወዳለ ደስታ እንዲደርሱ የሚያደርግ ነገር በማድረግና አሁን ያላቸውን ልምምድ በመለወጥ አዲስ የሆነ ነገርን በማምጣት ዓለምን ለማስደነቅ ጥልቅ ፍላጎት ያላቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የወቅቱ እውነት ቅድስና ግንዛቤ ሊሰጠው የሚገባውን ያህል ግንዛቤ ስላልተሰጠው በእርግጥ አሁን ያለውን ልምምድ የመለወጥ ከፍተኛ አስፈላጊነት አለ፤ ነገር ግን እኛ የምንፈልገው ለውጥ የልብ ለውጥ ነው፡፡ ይህ ሊገኝ የሚችለው እግዚአብሔር በረከቱን እንዲሰጠን በግል በመሻት፣ ኃይሉን እንዲሰጠን በመለመን፣ ጸጋው እንዲመጣልንና ባሕርያችን እንዲለወጥ ከልባችን ሆነን በመጸለይ ነው፡፡ ዛሬ የምንፈልገው ለውጥ ይህ ነው፡፡ ወደዚህ ልምምድ ለመድረስ የማይሰለችና ልባዊ ትጋትን መለማመድ ያስፈልገናል፡፡ --The Review and Herald, March 22, 1892. {2SM 23.2} Amh2SM 23.2