Go to full page →

የእውነት አሸናፊነት ChSAmh 226

ተጠራጣሪነት በአምላካዊው _ ሕግ ላይ ፌዝ፣ ሹፈትና ክህደት እንዲፈጸም መንስኤ መሆን ይችላል፡፡ የዓለማዊነት መንፈስ ብዙዎችን የመበከል፣ ጥቂቶችን ደግሞ የመቆጣጠር ኃይል አለው፡፡ አምላካዊው ተልዕኮ አመርቂ ውጤት ማምጣት እንዲችል ብርቱ ልፋትና የማያቋርጥ መሥዋዕትነት መከፈልቢኖርበትም—በስተመጨረሻ እውነት የከበረ ድል ባለቤት ይሆናል፡፡-- Prophets and Kings, p. 186. ChSAmh 226.4

የእግዚአብሔር ሥራ መደምደሚያ ላይ ትእዛዛቱ በምድር ዳግመኛ የከበረ ስፍራ ይይዛሉ፡፡ ሐሰተኛ ኃይማኖቶች ይሰራጫሉ፣ እርክስና ይሰፍናል፣ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፣ የቀራኒዮ መስቀል ከሰዎች ዐይን ይሰወራል፣ ድቅድቅ ጨለማ በመላው የምድር ገጽ ይሰራጫል፡፡ የወቅቱ ገናና ኃይላት በሙሉ በእውነት ላይ ይነሳሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ለመገርሰስ በሴራ ላይ ሴራ ይጎነጉናሉ፡፡ ነገር ግን እጅግ የከፋ ውድመት በሚደርስበት ሰዓት የኤልያስ አምላክ ሳይነገር በዝምታ መታለፍ የሌለበትን መልእክት በጽናት የሚያቀርቡ ሰብዓዊ መሣሪያዎቹን ያስነሳል፡፡ ዝና ባተረፉ የአገሪቱ ታዋቂ ከተሞችና ረጅም ርቀት ተጉዘው በልዑል እግዚአብሔር ላይ የተናገሩ ሰዎች ላይ ጽኑ የግሳጼ ድምጽ ይሰማል፡፡ ወንዶችና ሴቶች ፊታቸውን በሰው ከተቋቋመው ተቋም አንስተው በእውነተኛው ሰንበት ላይ እንዲያሳርፉ ልባዊ ጥሪ ይቀርብላቸዋል፡፡ Prophets and Kings, pp. 186, 187. ChSAmh 227.1