Go to full page →

ምዕራፍ 15—መከሩን መሰብሰብ ChSAmh 230

ግራ አጋቢው ችግር ChSAmh 230

ጌታ በቸርነቱ ከፊታችን እየቀደመ የሚከፍተውን የወንጌል በር የሚደግፍ በቂ ገንዘብ ማሰባሰብ የምንችለው እንዴት ነው? የሚለው ግራ አጋቢ ጥያቄ ለዓመታት ከፊታችን እየተንገዋለለ ኖሮአል፡፡ የወንጌልን እንቅስቃሴ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ለመተግበር አስፈላጊ የሆኑ ትእዛዛት በአምላካዊው ቃል ላይ በግልጽ ሰፍረው እናነባለን፡፡ የመለኮትን ጣልቃ ገብነት የሚያሳዩ አዎንታዊ አመላካቾችና ፍንጮች መሠራት የሚኖርበትን ሥራ በፍጥነት እንድንከውን በአንድነት ይገፋፉናል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 114. ChSAmh 230.1