Go to full page →

ከሰማይ የተላከ መልካም ዕድል ChSAmh 276

በአሜሪካ አንዳችም የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት የሌላቸው ወይም የተቀደሰውን አምላካዊ አስተምህሮ የማያውቁ፣ በባዕድ አምልኮ የሚመላለሱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጭ አገር ዜጎች አሉ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በቃሉ የተገለጸው የእውነት ተጽእኖ አርፎባቸው የአምላካዊው አዳኝ እምነት ወራሾች ይሆኑ ዘንድ ወደ እዚህ አገር መምጣታቸው ላይ የእርሱ እጅ ነበረበት፡፡Review and Herald, March 1, 1887. ChSAmh 276.2

እነዚህ ሰዎች እውነትን እንዲማሩና ለአገልግሎት ብቁ ሆነው እኛ ልንደርስባቸው ወደ ማንችላቸው ሕዝቦችና ቋንቋዎች አምላካዊውን ብርሐን እንዲያደርሱ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ቸርነቱ መጠን ከደጃፋችን አምጥቶአቸዋል፡፡Review and Herald, July 25, 1918. ChSAmh 276.3

ለዚህ ዘመን የተሰጠውን እውነት የመስማት ዕድል አግኝተው፣ አምላካዊውን እውነት ለሕዝቦቻቸው ለማድረስ የሚያስችላቸውን በቂ ዝግጅት አድርገውና ከእግዚአብሔር ዙፋን የሚፈነጥቀውን የከበረ ብርሐን ተሸክመው ወደ ምድራቸው የሚያደርሱአብዛኞቹ የውጭ አገር ዜጎች እነሆ በእግዚአብሔር በጎነት በአጠገባችን አሉ፡፡Pacific Union Recorder, April 21, 1910. ChSAmh 277.1

በአሜሪካ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ታማኝ ጥረት መደረግ ቢችል ሥራውን ወደ ፊት የሚያራምድ ታላቅ ጥቅም መገኘት በቻለ ነበር፡፡ ከእነዚህ ወንዶችና ሴቶች መሃል አንዳንዶቹ እውነትን ተቀብለው ብዙም ሳይቆዩ በዚህ አገር ለሚኖሩ ሕዝቦቻቸውም ሆነ በውጭ ለመሥራት ገጣሚዎች ናቸው፡፡ ምናልባትም ብዙዎች ወዳጆቻቸውን ለእውነት ለማሸነፍ ተስፋ በማድረግ ወደ መጡባቸው ስፍራዎች ይመለሱ ይሆናል፡፡ የሦስቱን መላእክት መልእክት ዕውቀት ለማካፈል ወደ ዘመዶቻቸውና ጎረቤቶቻቸው ሊያመሩ ይችላሉ፡፡Review and Herald, October 29, 1914. ChSAmh 277.2