Go to full page →

ምዕራፍ 24—ስኬታማ የክርስቲያን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የብቃት ማጎልበቻዎች ChSAmh 307

ቅልጥፍና (ብቃት) ChSAmh 307

ፈዛዛነትና የብቃት ማነስ ቅድስና አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር እየሠራን መሆኑን መገንዘባችን ለተቀደሰው መንፈሳዊ አገልግሎት ከቀድሞው እጅግ የበለጠ መነሳሳት እንዲያድርብን ያደርጋል፡፡ ይህ መረዳታችን ሕይወታችን በትጋት የተሞላ እንዲሆንና እያንዳንዱን ተግባር በብርታት እንድናከናውን ያስችለናል፡፡- Testimonies, vol. 9, p. 150. ChSAmh 307.1

ያለንበት ዘመን የላቀ ቅልጥፍናና ጥልቅ ቅድስና እንዲኖረን ይጠይቃል፡፡ ይህ ርዕሰ ጉዳይ አጥብቆ _ ስላሳሰበኝ ካንቀላፋችሁበት ተነስታችሁ የኃጢአት ሁሉ ሥር የሆነው ራስ ወዳድነት ከክርስቶስ መስቀል ጋር አብሮ የተሰቀለ ስብእና ያላቸውን ኃላፊነት የተላበሱ መልእክተኞች ለሥራ አሰማሩ” ስል ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 27. ChSAmh 307.2

የክፉው ኃይል በደቀ መዛሙርቱ ላይ ያስነሳ የነበረው ወጀብ ጥልቅና ጠንካራ ስለ ነበር ለእነርሱ ተሰጥቶ የነበረ አገልግሎት ከፍተኛ ብቃትና ቅልጥፍና የሚጠይቅ ነበር፡፡The Acts of the Apostles, p. 31. ChSAmh 307.3