Go to full page →

ሐቀኝነት፣ ታማኝነትና ትጋት ChSAmh 335

ለአንድ ሰው መንፈሳዊ ኃላፊነት ሲሰጥ ሊጠየቅ የሚገባው ጥያቄ አንደበተ ርቱዕ ነው ወይስ ባለ ጸጋ? የሚለው ሳይሆን ሐቀኛ ነው? ታማኝ ነው? የአገልግሎት ትጋት አለው? የሚል ሊሆን ይገባል፡፡ ግለሰቡ ያለ እነዚህ የብቃት መስፈርቶች የትኛውንም ዓይነት ክንውን ቢያገኝ ለማንኛውም ታማኝነት የሚጠይቅ ኃላፊነት ብቃት እንደ ጎደለው ተደርጎ ይወሰዳል፡፡Testimonies, vol. 4, p. 413. ChSAmh 335.3