Go to full page →

በለጋ ዕድሜ ChSAmh 40

የወንጌል አገልጋዩ ደግነትና መልካም እርዳታበታዳጊ ወጣቶች bያያዙና አቀባበሉ ይታይ፡፡ ታዳጊዎቹ ወንዶችና ሴቶች የጌታ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን ሁልጊዜ ያስታውስ፡፡ እነዚህ ለጌታ በጣም ቅርብ የሆኑና የከበሩ ቡቃያዎች በሚገባ ከተማሩና በግብረገብ ከታነጹ በለጋ ወጣትነታቸውም ቢሆን እርሱን ያገለግላሉ፡፡Testimonies, vol. 4, pp. 397, 398. ChSAmh 40.2

ወጣቶች በአገልግሎትም ሆነ በላፊነት ድርሻ ይኑራቸው እንጂ ችላ አይባሉ፡፡ ሌሎችን ለመባረክና ለመርዳት የበኩላቸው ድርሻ እንዳላቸው ይሰማቸው፡፡ ታዳጊ ወጣቶች አነስተኛም ቢሆን--እንደነርሱ ዓይነት ሁናቴ ላልተመቻቸላቸው የፍቅርና የምህረት መልእክት መስጠት ሊማሩ ይገባል፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 435. ChSAmh 40.3

ወላጆች ጊዜ ስላለው ዋጋና ጊዜን በትክክል ስለመጠቀም ልጆቻቸውን ሊያስተምሩ ይገባል፡፡ ለእግዚአብሔር _ ክብር የሚሆንና ሰብዓዊውን የሚባርh ተግባር መፈጸም የከበረ ዋጋ እንዳለው ያስተምሯቸው፡፡ ቀደም ባለው ለጋ ዕድሜያቸውም ቢሆን ለእግዚአብሔር ወንጌላዊ መሆን ይችላሉ፡፡- Christ’s Object Lessons, p. 345. ChSAmh 41.1