Go to full page →

አይቀሬው ፈተና ChSAmh 66

ጥቂት ታላላቅ ሰዎች በመጨረሻው የተከበረ አገልግሎት ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለራሳቸው በቂ የሆነ ነገር ያላቸውና ከእግዚአብሔር ይልቅ በራሳቸው ሃሳብ የሚመሩ በሆናቸው ጌታ ሊጠቀምባቸው አይችልም፡፡ ጌታ በብጠራውና በፈተናው ሰዓት ተገልጠው የሚታዩ ታማኝ አገልጋዮች አሉት፡፡ ጉልበቶቻቸውን ለበዓል ያላንበረከኩ አሁን ይፋ ያልወጡ ታማኞች አሉት፡፡ ምናልባትም በሰዎች ላይ በጉልv የሚያንጸባርቅ ብርሃን አይኖራቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእውነተኛ ክርስቲያን መለያ የሆነው ንጹህና ከልብ የመነጨ ጸባይ ውጫዊ ገጽታ የሚገለጠው ሥርዓተ 0ልበኝነትና የማያስደስት ሁናቴ በነገሠበት ሁናቴ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ በቀኑ ብርሃን ቀና ብለን ወደ ሰማይ ብንመለከት ከዋክብትን ማየት አንችልም፡፡ ሆኖም ዐይኖቻችን መለየት ተስኖአቸው እንጂ እነርሱ ግን በዚያው አሉ፡፡ ምሽት ላይ በታማኝነት ቦታቸውን ይዘው እያበሩ እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ ChSAmh 66.3

እያንዳንዱ ነፍስ የሚፈተንበት ጊዜ እሩቅ አይደለም. . . በዚv ወቅት በቤተ ክርስቲያን ወርቁ ከጉድፉ ይለያል፡፡ እግዚአብሔርን በትክክል መምስል--ከሚያብለጨልጨው የታይታ ገጽታ በጉልv ይለያል፡፡ በአብረቅራቂነታቸው ሲያስደምሙን የኖሩ አያሌ ከዋክብቶች በዚያን ወቅት የከሰሙና በጽልመት የተዋጡ ይሆናሉ፡፡ ግሩምና ያማረ የስንዴ ዛላ ካየንባቸው መድረኮች ሳይቀር ገለባው እንደ ደመና በንፋስ እየተነዳ ይወሰዳል፡፡ የሰማያዊውን መቅደስ የከበሩ ማስዋቢያዎች ብቻ እያሰቡ የክርስቶስን ጽድቅ ያልለበሱ በገዛ ራሳቸው አሳፋሪ ጽልመት ውስጥ ይወድቃሉ፡፡-Testimonies, vol. 5, pp. 80,81. ChSAmh 67.1