Go to full page →

ስንዴን ከእንhርዳድ መለየት ChSAmh 77

ብርቱ ውድመት የሚያስከትለው የአምላካዊው ፍርድ ወቅት እውነትን የመማር ዕድል ላላገኙ ወገኖች የምኅረት ጊዜ ነው፡፡ ምንም እንኳ የምኅረት ደጃፍ ለመግባት ፈቃደኞች ባልሆኑት ላይ ቢዘጋም ነገር ግን የማዳን እጁ አሁንም እንደተዘረጋችና ልቡ በምኅረት የተነካው ጌታ በፍቅር ዐይኖቹ እየተመለከታቸው ይገኛል፡፡. Testimonies, vol. 9, p. 97. ChSAmh 77.2

በቅርቡ እርሱን በሚያገለግሉና በማያገለግሉት መሃል የጦፈ ጦርነት ይነሳል፡፡ መናወጥ የሚችለው ማንኛውም ነገር ይናወጣል--የማይናወጠው ደግሞ በዚያው ባለበት ይጸናል፡፡--Testimonies, vol. 9, pp. 15, 16. ChSAmh 78.1

በሕዝቦች ላይ ጥርጣሬና መደናገር በሚደርስበት ወቅት አማላይ ተጽእኖ ላለው ዓለምና ለሰይጣን አገልግሎት ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ ያልሰጡማንነታቸውን በእግዚአብሔር ፊት ትሑት አድርገው በሙሉ ልባቸው ለእርሱ የተገዙ፣ በፊቱ ተቀባይነትና ይቅርታ ያገኙ ብዙዎች ይኖራሉ፡፡-- Testimonies, vol. 1, p. 269. ChSAmh 78.2

መጽሐፍ ቅዱስን እያነበቡ ነገር ግን የቃላቱን እውነተኛ ሐሳብ ማስተዋል የተሳናቸው አያሌዎች አሉ፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ ወንዶችና ሴቶች ሰማያዊውን መንግሥት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ አምላካዊውን የብርሐን ጨረር፣ ጸጋና መንፈስ ቅዱስ የሚናፍቁ ነፍሳት ዕንባና ልመና ሽቅብ ወደ ሰማይ ይተማል፡፡ ብዙዎች በአምላካዊው ቅጥር ለመሰባሰብ እየተጠባበቁ በሰማያዊው መንግሥት አፋፍ ላይ ይገኛሉ፡፡-The Acts of the Apostles, p. 109. ChSAmh 78.3