Go to full page →

ክርስቲያኑ የሚከተላቸው መርኅዎች ChSAmh 146

ሰይጣን ከሰልፋችን እንዳያዘናጋን የማንፈቅድ እስከሆነ ድረስ በክርስትና ሕይወታችን አክብረን ልንቀበላቸው የሚገቡ ሦስት መርኅዎች አሉ--መትጋት፣ መጸለይና መሥራት፡፡--Testimonies, vol. 2, p. 283. ChSAmh 146.2

ከhርስቶስ ጋር ቃል ኪዳን ያለው ማኛውም ነፍስ በሚቻለው ንቁ፣ ቅንአት ያለውና ውጤታማ መንፈሳዊ ሠራተኛ ለመሆን ራሱን ለጌታ አገልግሎት አሳልፎ ሰጥቶአል፡፡ ክርስቶስ እያንዳዱ ሰው የተጣለበትን ኃላፊነት ሲወጣ ለመመልከት እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ በእያንዳንዱ የአገልግሎት እርከን የሚገኙ አገልጋዮቹ ይህን መርኅ የሚከተሉ ይሁኑ፡፡--Testimonies, vol. 5, p. 460. ChSAmh 146.3