Go to full page →

ወደ ሕዝቦች ሂዱ ChSAmh 168

ነፍሳትን ባሉበት መድረስ እንጂ ወደ እኛ እስኪመጡ መጠበቅ የለብንም፡፡ አምላካዊው ቃል ለጉባዔ መቅረቡ የአገልግሎቱን መጀመር የሚያሳይ ቢሆንምወገኖች ያሉበት ድረስ ካልሄድን በቀር የወንጌልን መልእክት ፈጽሞ መስማት የማይችሉ አያሌዎች አሉ፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 229. ChSAmh 168.1

የወንጌል ተልዕኮ ታላቁ የክርስቶስ መንግሥት ሕገ መንግሥት ነው፡፡ ደቀ መዛሙርት የምኅረት ግብዣ የሆነውን ጽኑ አገልግሎት ለሁሉም ነፍሳት መስጠት ነበረባቸው፡፡ ሰዎች ወደ እነርሱ እንዲመጡ ሳይጠብቁ መልእክቶቻቸውን ይዘው ነፍሳት ወዳሉበት መሄድ ነበረባቸው፡፡The Acts of the Apostles, p. 28. ChSAmh 168.2