Go to full page →

የድጋፍ ስሜት ማሳየት ChSAmh 170

ትኩረታችንን ሕይወትን በብዙ ውጣ ውረድ እየተፋለሙ በሚገኙ ወገኖች ላይ ማድረጋችንና ለእነርሱ አጭር ጊዜ መስጠታችን እንዲታደሱና እንዲበረታቱ ይረዳቸዋል፡፡ አንዳችም ወጪ የማያስወጡ እንደ ዋዛ የሚነገሩ ደግ ቃላቶችና መጠነኛ ትኩረት ያቺ ነፍስ ከከበባት የፈተናና የጥርጣሬ ደመና ፋታ እንድታገኝ ያስችላታል፡፡ በክርስቶስ ዓይነት ርኅራኄ የተገለጠው ግልጽና ቀጥተኛ የሆነው እውነተኛ ልብ ስስ እና አደጋ የማይችለውን የልብ ደጃፍ የመክፈት ኃይል አለው : :- Testimonies, vol. 9, p. 30. ChSAmh 170.3

ቀላልና ውስብስብ ያልሆነ ትሁት አካሄድ ተጠቅመን በሺ ወደ ሚቆጠሩ ነፍሳት መድረስ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔርን ከሚወድ፣ ስለ አምላካዊው ፍቅር ማውራት ተፈጥሮው ከሆነ ሰው ልብ የሚፈሱት ቀላልና ግልጽ ቃላት ዓለም በችሎታቸው ለምታደንቃቸው እጅግ በሳል ማስተዋልናየወንጌል አገልግሎት የምንሰጥባቸው ዘዴዎች ተሰጥኦ ላላቸው ወንዶችና ሴቶች ታደሰ ሊያመጣላቸው ይችላል፡፡ በቂ ዝግጅት ያደረግንባቸውና ያጠናናቸው ቃላት ብዙውን ጊዜ ያን ያህል አመርቂ ተጽእኖ ሲያሳድሩ አይታዩም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች ተፈጥሮአዊ በሆነ ቀላል አቀራረብ አንደበታቸው የሚያወጧቸው እውነተኛና ታማኝ ቃላት ለረጅም ጊዜያት ተከርችመው የነበሩ ልቦችንይከፍታሉ፡፡ Testimonies, vol. 6, p. 115. ChSAmh 170.4