Go to full page →

አዎንታዊውን እውነት መያዝ ChSAmh 174

እውነትን የማቅረብ ምኞት ሲያድርብን ብዙውን ጊዜ ተቃውሞ ይገጥመናል፡፡ ሆኖም የቀረበውን ተቃውሞ በክርhር የመፍታት ፍላጎት ካደረብን ችግሩን ከማባባስ ውጪ የምንፈይደው አይኖርም፡፡ አዎንታዊውን ነገር ይያዙ፡፡ ከርhር ለመግጠም ያልፈለጓቸውን የተቃዋሚዎችዎን ልብ እንዴት መንካት እንደሚገባ የሚያስተውሉት የእግዚአብሔር መላእከት ይመለከቶታል፡፡ ከተቃዋሚዎች በሚነሱ አሉታዊ ነጥቦችና ጥያቄዎች ላይ ለመነጋገር በመሞከር ፋንታ አዎንታዊዎቹን እውነቶች ወደ አእምሮዎ በመሰብሰብ በጽኑ ጸሎትና የልብ ቅድስና ያስተሳስሯቸው: -Testimonies, vol. 9, pp. 147, 148. ChSAmh 174.1