Go to full page →

ከመለኮት ጋር በትብብር መሥራት ChSAmh 185

የእያንዳንዱ ሰው ሥቃይና ዋይታ ክርስቶስን ይሰማዋል፡፡ ርኩስ መንፈስ ሰብዓዊውን ወሰን ጥሶ ሲገባ እርግማኑና ጉስቁልናው ከርስቶስን ይሰማዋል፡፡ የሰው አካል በትኩሳትና በህመም ሲነድ ሥቃዩ ክርስቶስን ይሰማዋል፡፡ ስለዚህ የሱስ በዚህ ዓለም ሲመላለስ እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም ህሙማንን ለመፈወስ ፈቃደኛ ነው፡፡ የክርስቶስ አገልጋዮች የእርሱ ወኪሎችና ሥራውን የሚያከናውንባቸው መሣሪያዎቹ ናቸው፡፡ የሱስ የመፈወስ ኃይሉን በአገልጋዮቹ አማካይነት ሊሠራበት ይፈልጋል፡፡The Desire of Ages, pp. 823, 824. ChSAmh 185.2

እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ አማካይነት የታመሙ፣ አሳዛኝ ሁናቴ ላይ ያሉና በክፉ መንፈስ የተያዙ ድምጹን እንዲሰሙ ያደርጋል፡፡ ሰብዓዊ ወኪሎቹን ተጠቅሞ ዓለም አይቶት የማያውቅ አጽናኝ ለመሆን ምኞቱ ::-- The Ministry of Healing, p. 106. ChSAmh 185.3

ክርስቶስ በወንጌላዊ የሕhምና አገልግሎት ከሚሳተፉ ጋር ተባብሮ ይሠራል፡፡Testimonies, vol. 7, p. 51. ChSAmh 185.4

ጌታ በእነርሱ ውስጥ ስለሚሠራ በሄዱበት በሽተኞችን ይፈውሳሉ፣ ወንጌልን ለድኾች ይሰበካሉ፡፡The Acts of the Apostles, p. 106. ChSAmh 185.5

ክርስቶስ በምድር ይመላለስ እንደነበረው በአካል ወደ ከተሞቻችንና መንደሮቻችን መጥቶ በሽተኞችን ባይፈውስም፤ እርሱ የጀመረውን የወንጌላዊ ሕክምና አገልግሎት የምንቀጥልበትን ተልዕኮ ሰጥቶናል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 168. ChSAmh 185.6