Go to full page →

ለወንጌል መልእክተኛነት የሚረዳ ትምህርት GWAmh 45

«የእግዚአብሔር ናችሁ፣ የእግዚአብሔር ሕንፃዓ ናችሁ፣ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንፍ” (፲ኛቆሮ. 3፡9) የክርስቲያን ወንጌላዊ ሥራ ቀላል አይደለም፡፡ ወይም የማይፈለግ አይደለም፡፡ ለሕይወቱ ዘመን ሁሉ የሚያቆየው ብዙ ሥራ ተደቅኖለታል፡፡ ለእንደዚህ ያለ ሥራ የሚሰለፍ ሰው ኃይሉን በሙሉ በሥራው ላይ ማዋል አለበት፡፡ ከፍ አድርጐ ማለም አለበት፡፡ ከዚህ ከፍተኛ ዓላማ የበለጠ ታላቅ ደረጃ የለም:: ሳይቀበል የብርሃንን ፀዳል ሊያበራ የሚችል የለም:: መምህር ለመሆን የሚያስችለውን ፀጋ ከመቀበሉ በፊት ተማሪ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ; አባሪ ሠራተኞቹ እንዲሆኑ ከመረጣቸው የተቀደሰውንና ከፍተኛውን ዕውነት ለማዳረስ ታላቅ ዝግጅት ያስፈልጋል፡፡ በጥበብ ያገለግሉ ዘንድ የተሰለፉ ሰዎች በአንድ ጊዜ ከመሰላሉ ጫፍ ላይ ለመውጣት መከጀል የለባቸውም፡፡ ከሥር ጀምረው ደረጃ በደረጃ መውጣት አለባቸው፡፡ GWAmh 45.1

የማጓጓል ዕድልና መብት አላቸው፡፡ ባሰ ኃይላቸው የአምላክን ሥራ ተቀባይነት ባለው መንገድ ለመሥራት መሞከር አለባቸው:: ወንጌላዊያን በየትኛውም ክፍለ ዓለም ቢሠሩ ወጣቶችን ለታላቁ የአምላክ የጦር ሜዳ ብቁ ሆነው እንዲገኙ ማነቃቃት አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን የሚሉ ሁሉ አቢይ ሥራ እንዳለባቸው መገንዘብ አለባቸው፡፡ አገልጋይ የሚለው ቃል ራሱ መቀጠርን፣ ሥራንና ኃላፊነትን ያመለክታል፡፡ ማንኛውም ሰው በሥራው ውስጥ ተቀጥሮ ያገለግል ዘንድ አግኪአብሐር ለሁሉም ኃይል ሰጥቶታል፡፡ ለሁሉ ሥራ ስላዘጋጀለት ሁሉም ሰው ማንኛውንም የአካል ክፍሉን ለሥራ ሊኮተኩት ይገባዋል፡፡ GWAmh 45.2