Go to full page →

መ - ለሰዎች ጽናት ምሣሌዎች GWAmh 11

የእግዚአብሔር ሰዎች በዓለም ዘንድ ታዋቂነትና ክብር አያገኙም፡፡ እስጢፋኖስ ስለተሰቀለው ክርስቶስ ማስተማሩ ከነውር ተቆጥሮበት በደንጊያ ተወግሮ ሞተ፡፡ ጳውሎስ ለአህዛብ በመመስከሩ፤ ታሠረ፣ ተደበደበ በመጨረሻም ተገደለ፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ «ስለጌታ ራዕይ ስለእግዚአብሔር ቃል» በጳጥሞስ ደሴት እነዚህ በመለኮት ኃይል ተደግፈው የጽዋችን ጽናት የሚያመለክቱት ደግኖች እግዚአብሔር ተስፋውን አንደማይረሳና ከሰዎች አንደማይርቅ ማስረጃዎች GWAmh 11.2

የሰዎችን የወደፊት የግብረ-ገብ ጉድለት የሚያደፋፍር አንድም የኃጥዓን ማስረጃ የለም፡፡ ታላቅ የጦር አለቃ ዓለምን አንቀጥቅጦ ቢገዛም ፍጻሜው አሥራትና ተስፋ ቆርጦ መሞት ነው:: ታላቁ ፈላስፋ በፍልስፍናው የሰዎችን ሀሳብ ካናወጠ በኋላ በሚመራመረው ዓለም ውስጥ የእግዚአብሔርን የበላይነት ሳያውቅ ይሞታል፡፡ «አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው አንደሚጠፉ አንስሶች ነው፡፡ GWAmh 11.3

ነገር ግን የእግዚአብሔር የሃይማኖት ጀግኖች ከምድር ሁሉ ሐብት የበለጠ ፀጋ ይወርሳሉ፡፡ በዓለም ዘንድ ባይታወቁምና ባይከበሩም በመዝገብ መጽሐፍ የሰማይ ዜጐች ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ የዘለዓለም ክብር ይጐናጸፋሉ፡፡ GWAmh 11.4

የሰዎች ዋናው ተግባር ኃጢዓተኞችን ወደ እግዚአብሔር በግ ማመላከት ነው፡፡ ዕውነተኛ አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ሀሳብ ከፍጻሜ ለማድረስ ተባባሪ ሠራተኞቹ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሄዱና ስለክርስቶስ አስተምሩ ይላቸዋል፡፡ ምህረቱ፣ ደግነቱንና ፀጋውን ለማያውቁት አስረዱ ይላቸዋል፡፡ GWAmh 11.5

«እንግዲህ ያላመኑበት እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያላስተማሪስ እንዴት ይሰማሉ?” ፤ መዝሙር 49:20፡፡ GWAmh 12.1

«የምሥራች የሚናገር፤ ሰላምንም የሚያጠራ፤ የመልካምንም የምሥራች የሚናገር መድኃኒትንም የሚያወራ ጸዮንንም አምላክሽ ነግሶአል የሚል ሰው አግሩ በተራሮች ላይ በጣም ያማረ ነው፡፡ እናንት የየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷልና የሩሣሌምንም ታድጓልና ደስ ይበላችሁ:: በአንድነትም ዘምሩ የእግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንድን በአህዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፡፡ በምድርም ዳርቻ የሚኖሩት ሁሉ የአምላካችን መድኃኒትነትን ያያሉ» GWAmh 12.2

የእግዚአብሔር ሠራተኞች «ሥራችን አይሳካልን ይሆን? » ብስው መጨነቅ አይገባቸውም፡፡ የሱስ ጌታ ረዳታችን ነው:: መንፈሱ ያነቃቃናል፡፡ ራሳችን ካስረከብን መጠን ወሰን የሌለውን ፀጋውን ያጐናጽፈናል፡፡ GWAmh 12.3