Go to full page →

አዲስ የሥራ መስክ (ቦታ) GWAmh 73

አዲስ የሥራ ቦታ ስትገባ የመጣህበትን ዓላማ በአንድ ጊዜ አትናገር፡፡ GWAmh 73.5

ስባተኛውን ቀን ሰንበት እናከብራለን፡፡፡ በትንሣኤ እናምናለን:: ሰባተኛውን ቀን አክባሪ እንባላለን ብሎ ማንነትን በአንድ ጊዜ ማስተዋወቅ ለግንኙነት ገደብ አንደመፍጠር ይቆጠራል፡፡ ልዩነትን በማያስከትሉ ነገሮች ላይ መጀመሪያ መነጋገሩ ይበጃል፡፡ በምሣሌነት መልካም ክርስትናን ማሳየት በጣም ጥሩ ነው፡፡ እንደምትወዳቸው፣ ሰላምን ወዳድ መሆንህን በክርስትና መንገድ አሳያቸው፡፡ ለሰዎች አሳቢ ቅን የወንገል አገልጋይ መሆንህን ይገንዘቡ፡፡ ከዚያ በኋላ አንዲያምኑህ ስታደርግ ለማስተማር ዕድል ያጋጥምሀል፡ GWAmh 73.6

ጥበቡን የሚሹትን እግዚአብሔር አይረሳቸውም፡፡ ጊዜ ይግጠመን አያልን ተቀምጠን ከመጠበቅ ይልቅ መልካም ጊዜ አንድናገኝ መጣር ይሻላል፡፡ ወንጌላዊው ልቡን ከአምላክ ጋር በጸሎት ካስተባበረ አምላክ የሚናገረውን ትክክለኛ ቃል ያቀብለዋል፡፡ GWAmh 74.1

ሌሎችን ለማረም የምንሰነዝራቸው ቃላት ምርጥ መሆን አለባቸው፡፡ የሞት ወይም የሕይወት ሽታ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶች ለተግሣፅና ለዘለፋ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ድሎት ያለውን ሰው ከማሻሻል ይልቅ ያብሱታል፡፡ እውነትን ለሰዎች ለማብሠር ተሰለፉ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ዘይት የለዘበ ፍቅር ያስፈልጋቸዋል።፡ ምንም ጊዜ ቢሆን ተግሣፅን የሚሠጡ ሰዎች ፍቅር ያልተለያቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ ያን ጊዜ የተሰነዘረው ምክር ከማባባስ ይልቅ ያሻሽላል፡፡ የራሱ ሥራ ነውና ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ኃይልና ችሎታውን ያቀብለናል፡፡ GWAmh 74.2