Go to full page →

የዕለት ኑሮ GWAmh 89

ወንጌላዊ ለሥራው ብቁ ሆኖ ይገኝ ዘንድ ኑሮው ያልተደናገረና ግልጽ መሆን አለበት፡፡ ሕይወቱ ራስን የመግታት ኑሮ ያሳይ ዘንድ ጸሎትኛና ለክርስቶስ ያደረ መሆን አለበት:: ንግግሩ የተጣመመ ሐረግ የሌለበት የተጣራና ከንፈሮቹን ትርጉም የሌለው የማይረባ ቃል የማይነካው መሆን አለበት: አለባበሱ ከሥራው ጋር የሚስማማ የጨዋ አለባበስ መሆን ይገባዋል፡፡ መምህራንና ወንጌላዊያን በመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጣቸውን የኑሮ ደረጃ ለመድረስ ይጣሩ፡፡ ያልተፈለጉ መስለው የሚታዩትን ጥቃቅን ነገሮች አይናቁ፡፡ ጥቃቅን ነገሮችን መናቅ ከፍተኛ ኃላፊነትን ችላ ወደ ማለት ያደርሳል፡፡ GWAmh 89.2

በጌታ የወይን ቦታ የሚሠሩ ገበሬዎችን የሚያደፋፍር ዘለዓለማዊ ምሣሌ አላቸው:: የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመልአክት አገልግሉት፣ የክርስቶስ ርህርሄና ነፍሳትን የማዳን ክቡር ተስፋ አይለያቸውም፡፡ «ጥበበኞች እንደሰማይ ጸዳል፣ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ አንደ ከዋክብት ለዘለዓለም ይደምቃሉ፡፡›» GWAmh 89.3