Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሰዎችን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ማመልከት

    የተጻፉት ምሥክሮች አዲስ ብርሃን እንዲሰጡ አይደለም፤ ነገር ግን ካሁን ቀደም የተገለጸውን በፈንፈስ የተጻፈውን እውነት አጥልቆ በልብ ውስጥ ለማሳተፍ ነው፡፡ ሰው ላምላክና ለባልንጀሮቹ የሚያደርገው ተግባር በአምላክ ቃል ውስጥ የተገለጸ ሁኖ ተወሰቷል፤ ነገር ግን ጥቂቶቻችሁ ብቻ ለተሰጠው በርሃን ታዛዦች ናችሁ፡፡ ተጨማሪ እውነት የሚቀርብ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሥክሮች አማካይነት ካሁኑ ቀደም የተሰጠውን እውነት አብራርቷል፤ ራሱ በመረጠውም መንገድ ለማነቃቃትና ለሐሳባቸው ሊያሳትፍላቸው በሰዎች ፊት አቅርቦላቸዋል፤ ሁሉም ያለ ምክንያት ይሆኑ ዘንድ፡፡ ምሥክሮች ያምላክን ቃል ትንሽ ለማድረግ (ለማቅለል) አይደለም፤ ዳሩ ግን ከፍ እንዲያደርጉትና ሐሳብንም ወደርሱ እንዲሰጡ ነው እንጂ ያማረው የእውነት ግልጽነት (ማብራሪያ) ለሁሉ ይሳትፍለት ዘንድ፡፡ ፪25T665;CCh 144.1

    ቅዱሣት መጽሕፍት ያምላክ ቃል ትምህርትና ሁኔታው ሁሉ የሚፈተንበት ሕግ እንደሆነ በግልጽ ስለሚናገሩ መጽሐፍ ቅድዱስን ለማስወገድ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠ አይደለም፤ ወይም ሊሰጥ አይቻልም… ኢሳይያስ ‹ወደ ሕግ ወደ ምሥክርም እንዲህ ያለ ነገር ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም› ሲል ይናገራል፡፡ (ኢሳይያስ ፰፡፳)፡፡፫3GC.................7;CCh 144.2

    ‹ወንድም ጄ በምሥክሮች አማካይነት የተሰጠው በርሃን ያምላክ ቃል ተጨማሪ እንደሆነ ለማስመሰል በመሻቱ ሐሳብን ለማደናገር ፈልጎዋል፤ ነገር ግን በዚህ ነገሩን በአሰት ብርሃን ማቅረቡ ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህ አኳኋን የሕዝቡን ሐሳብ ወደ ቃሉ ለመሳብ፤ ስለርሱም በይበልጥ አብራርተው እንዲያስተውሉ የተስማማ /የተገባ/ መሆኑን አይቶአል›፡፡ የምላክ ቃል እጅግ የጨለመበትራ አእምሮ ለማብራራት በቂ ነው ሊያስተውሉትም ፍላጎት ያላቸውም ሊያስተውሉት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህም ሆኖ ያምላክን ቃል ጥናታቸው ለማድረግ አፍዓውያን የሆኑ እጅግ ግልጽ የሆኑትን ትምህርቶቹን በቀጥታ በመቃወም የሚኖሩ ሆነው ይገኛሉ፡፡ እንግዲህ ወንዶችም ሴቶችም ያለ ምክንያት እንዲሆኑ ሊያደርጋቸው እግዚአብሐር ግለጽ የሆኑትን የተመለክቱትን ምሥክሮች ይሰጣቸዋል፤ ለመከተልም ችላ ወዳሉትም ቃል መልሶ ያመጣቸዋል፡፡ ያምላክ ቅል ትክክለኛ (የቀናውን) የሆነውን የአኗኗር ልምዶች ለማበጀት ጠቅላላው ፕሪንስፕሎች የተመሉበት ነው፤ ምስክሮችም በጠቅላላም ሆነ ለየግለ ሰብ የቀረቡት በተለይ ሐሳቦቸውን ወነዚህ ፕሪንስፕሎች በይበልጥ ለመሳብ የተሰቡ ናቸው፡፡CCh 144.3

    የተከበረውን መጽሐፍ ቅዱስ ወሰድሁና ለእግዚአብሐር ሕዝብ ለቤተክርስቲ ያኒቱ ከተሰጡት አያሌዎች ምሥክሮች ጋር አጣመርሁት እዚህ ላይ አልሁ የሁሉም ጉዳዮች ሁሉ የሚጋጠሙት ነው፡፡ የሚርቁት ኃጢአት ተመልቶላቸዋል፡፡ የሚፈልጉትም ምክር ለሌሎች ጉዳዮች የተሰጠው እንዲሁም ለራሳቸው ሆኖ የቀረበው እዚህ ላይ ሊገኝ ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር መሥመር በመስመር ትእዛዝ በትእዛዝ ሊሰጣችሁ ተደስቷል፡፡CCh 144.4

    ነገር ግን በምስከሮች ውስጥ ያሉትን በእርግጥ የሚያውቁ ከናንተ ብዙዎች አይደሉም፡፡ ከቅዱሣት መጽሕፍት ጋር የተላመዳችሁ አይደላችሁም፡፡ ወደ መጽሕፍ ቅድስ ደረጃ (አቋም) ለመድረስና ክርስቲያናዊ ፍጹምነትን ለማግኘት ፍላጎት ኑሮዋችሁ የምላክን ቃል ጥናታችሁ አድርጋችሁ ብትሆኑ ኑሮ፤ ምስክሮች ባላሻችሁም ነበር ለመታዘዝ ችላ ወዳላችሁ በመንፈስ ወደ ተጻፉት ቃላት እያሳሰባችሁና ንጹህና ከፍ ካሉት ትምህርቶቹ በመስማማት ሕይወታችሁን ጋንጹ ዘንድ እየለመናችሁ ግልጽ በሆኑት፤ በቀጥታ በተመለከቱላችሁ ምስክሮች ሊደርስባችሁ የፈለገው፤ ከተጻፈው ያምላክ መጽሐፍ ጋር ራሳችሁን ለማስተዋወቅ ችላ ስላላችሁ ነው፡፡ ፬45T 663-665;CCh 145.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents