Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፳፩—መጽሐፍ ቅዱስ

    በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከፈላጊው የተሰወሩ የእውነት ዕንቁዎች አሉ፡፡ የእውነት ማዕድን ከቶ ማለቂያ የለውም፡፡ በትሁት ልቦና ቅዱሳት መጽሕፍትን ይበልጡን ስትሻ ይባልጡን ትደስትበታለህ፤ እንደ ጳውሎስም፤ ‹የጥበቡ ጥልቅ ሆይ የባለጸግነቱም የእግዚአብሔር እውቀት ፍርዱም ሆይ የማትገኝ መንገዱም የማትመረመር› እያልህ ጩኸት እንደ መናገር ይሰማሃል፡፡ (ሮሜ ፲፩፡፴፫)15T266;CCh 151.1

    ክርስቶስና ቃሉ በፍጹም የሚሰማሙ ናቸው፡፡ ከተቀበሉትና ከታዘዙት ከርስቶስ በብርሃንም እንዳለ በብርሃንም ለመሔድ ፈቃደኞች ለሆኑት ሁሉ ለእግሮቻቸው የተረጋገጠ መንገድ ይከፍትላቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ቃሉን ቢወዱ በዚህ ታች ባለችው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰማይ በኖረን ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ቃልን ለመሻት የሚናፈቁ የሚራሱም ይሆኑ ነበር ቅዱሳት መጽሕፍትን ከቅዱሳት መጽሕፍት ጋር ለማመዛዘንና ቃሉን ያስቡበት ዘንድ በየጊዜው ናፋቂዎች ይሆናሉ፡፡ ለጧቱ ወረቀት ለጋዜጣዎች ወይም ዜናዎች ይልቅ ለቃሉ ብርሃን በጣም ናፍቂዎች ይሆናሉ፡፡ እጅግ ታላቅ የሆነው ፍላጎታቸው ያምላክን ልጅ ሥጋ መብላትና ደሙን መጠጣት ነው፡፡ ውጤቱም ሕይወታቸው ከቃሉ ፕሪንሲፕልና ተስፋዎች የሚስማማ ይሆናል፡፡ ምክሩም /ትምህርቱም ለነሱ እንደ የሕይወት ዛፍ ቅጠሎች ይሆናል፡፡ በነሱም ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የማመነጭ የውኃ ጉድጓድ ይሆናል፡፡ የሚያለመልም የጸጋ ጐርፎች ነፍስን ያለመልማል፤ ያነቃቃልም፤ ያበረቱዋቸዋል፤ ያደፋፍሩዋቸዋልም፡፡ ፪28T193; CCh 151.2

    ሰፋ ባለው በዓይነተኛነቱና በሚያቀርበው የጉዳዮቹ አቋም መጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብን ሁሉ የሚያስደስትበትና ለልበም ሁሉ የሚማፀንበት አንዳች ነገር አለው፡፡ በገጾቹ ውስጥ በጣም ጥንታዊ የሆነ ታሪክ በጣምም እውነተኛ የሆነ የሕይወት ታሪክ ለመንግሥትም አስተዳደር የሆኑ ሥነ ሥርዓቶች /ፕሪንሲፕሎች/ ለቤተሰብም ሥርዓት የሆነ ፕሪንስፕል ይገኝበታል፤ ይኸውም ሰብዓዊ ጥበብ ካሁኑ ከደም ከቶ የልተስተካከለው ፕሪንሲፕሎች ናቸው፡፡ በጣም የጠለቀ ፊሎሶፊ. እጅግም ጣፋጭና ከፍ ያለ እጅግም የተወደደና የሚያነቃቃ ቅኔ አለበት፡፡ በእንዲህ ሲታሰብ እንኳ ከማናቸውም ደራሲ ድርሰት በዋጋነት የማይገመት ብልጫነት ያላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ከታላቁ ዋናው ሐሳብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ስንመለከት ወሰን የሌለው ሰፋ ያለ ዓላማ ወሰንም የሌለው ታላቅ ዋጋነት ያላቸው ናቸው፡፡ በዚህ ሐሳብ ብርሃን ስንመለከት ርእስ አንቀጹ ሁሉ አዲስ ፍች አለው፡ እጅግ ግልጽ ሆኖ በተነገረው እውነት ውስጥ እንደ ሰማይ ከፍ ያሉና ዘላለማዊነትን የሚጠቀልሉ ፕሪንሲፕሎች አሉበት፡፡ ፫3ED 125; CCh 151.3

    ከቅዱሳ መጻሐፍት አንዳች አዲስ ነገር በየቀኑ መማር አለብን፡፡ የዘላለም ሕይወት ቃላት አለባቸውና እንደ ተሠወረ መዝገብ እሻቸው፡፡ እነዚህን የተቀ ደሱ ጽሁፎች ለማስተዋል፤ ጥበብና ለማስተዋል ጸልይ፡፡ ይህን ብታደርግ በአምላክ ቃል ውስጥ አዳዲስ ክብሮች ታገኛለህ በእውነት ጋር ተያይዘው ስላሉት አርዕትቶች አዲስና የተከበረ ብርሃን እንደ ተቀበልህ ይሰማሃል ቅዱሣት መጻሕፍት በግምትህ ዘንድ አዲስ ዋጋነት ዘወትር ያገኛሉ፡፡ ፬45T266; CCh 151.4

    የመጽሐፍ ቅድስ እውነት ቢቀበሉት ሐሳብን ከምድራዊነትና ከውርደት ከፍ ያደርገዋል፡፡ ያምላክ ቃል እንደሚገባ ሱከበር፤ ወጣቶችም ሽማግሎችም ፈተናን ለመቃወም የሚያስላቸው ውስጣዊ ቅንነትና የፕሪንሲፕል ኃይል ያገኛሉ፡፡ ፭58T319;CCh 152.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents