Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አማኝ በንግድ ሥራ ደግ መሆን አለበት፡፡

    የታመነ ሰው በክርስቶስ ግምት ዘንድ ጠማማነት የሌለበት ቅንነትን የሚገልጽ ነው፡፡ የማታለል ክብደትና የአሰት የሚዛኖች ብዙዎች ጥቅሞቻቸውን ለማስፋፋት የሚሹበት በአምላክ ፊትየተጠሉ ናቸው፡፡ ሆኖም ያምላክን ትእዛዛት እንጠብቃለን የሚሉ በአሰት ስፍርና (ክብደትና) በአሰት ሚዛኖች የሚሰሩ ናቸው፡፡ ሰው በውነቱ ከአምላክ ጋር ግንኙነት ሲያደርግና በውነት ሕጉነ ሲጠብቅ ሕይወቱ እውነትን ይገልጻል፡፡ አድራጎቶቹ ሁሉ ከክርስቶስ ትምህርቶች የሚስማማ ይሆናልና፡፡ ለትርፍ ብሎ ክብሩን አይሸጥም፡፡ የርሱ ፕሪንሲፕል በተረጋገጠው መሠረት ላይ ይገነባል በዓለማዊ ጉዳዮች ረገድ ዓመሉም የርሱ ፕሪንሲፕል ቅጅ ነው፡፡ ጽኑ ቅንነት በዓለም አሰርና ቆሻሻ መኻከል እነደ ወርቅ ያበራል፡፡CCh 158.2

    ማታለል አሰትና አለመታመን እያጭበረበሩበት ከሰው ዓይኖች ይሠወሩ ይሆናል ከአምላክ ዓይኖች ግን የሚሰወሩ አይደለም፡፡ ያምላክ መላእክት የጠባይን መሻሻል ሚጠባበቁና የግብረገብን ዋጋነት የሚመዝኑ ስለ ጠባይ የሚገልጹ እኒህን ድርጊቶች በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ ይመዘግባሉ፡፡ ሰራተኛው በሕይወት ዕለታዊ ሥራዎቹ ያልታመነ ቢሆንና ሥራውን ቢያቃልል ዓለም በስራው ደረጃ መሠረት በሃይማኖት ረገድ ያለውን ደረጃ ቢገምት ልክ መፍረዱ ነው፡፡CCh 158.3

    የሰው ልጅ በሰማይ ደመና በቅርቡ መምጣቱን ማመን እውነተኛውን ክርስቲያን በተለመደው የሕይወት ሥራው ችላ ባይና የማይጠነቀቅ አያደርገውም፡፡ ስለ ክርስቶስ በተሎ መገለጽ የሚጠባበቁ ሰዎች ሰነፎች አይሆኑም በስራ ትጉዎች ይሆናሉ እንጂ፡፡ ሥራቸውን ባለመተንቀቅና ባለመታመን አያደርጉትም ነገር ግን በታማኝነት በቀልጣፋነትና በሐቀኝነት ነው፡፡ ለዚህ ሕይወት ነገሮች ባለመጠንቀቅ ከቁም ነገር አለመቁጠር የመንፈሳዊነታቸውና ከዓለም የመለየታቸው ማስረጃ እንደሆነ ራሳቸውን የሚደልሉ በትልቅ መታለል ውስጥ ናቸው፡፡ እውነተኝነታቸው ታማኝነታቸውና ቅንነታቸው በሥጋዊ (በጊዜያዊ) ነገሮች የሚፈተንና የሚታወቅበት ነው፡፡ በትናንሹ ታማኞች ከሆኑ በብዙም ታማኞች ይሆናሉ፡፡ ብዙዎች ፈተናውን ለመቻል የሚያቅታቸው በዚህ ላ መሆኑ ታየኝ፡፡ የጊዜየዊ ግዳጅነታቸውን በማካሔዳቸው ላይ እውነተኛ ጠባያቸውን ብቅ ያደርጋሉ፡፡ ለጓደኞቻቸው በሚያደርጉት አለመታመንን ተንኮልን እያሰቡ የማይታመኑ መሆናቸውንም ይገልጻሉ፡፡ የወደፊቱ ይዞታቸው የማጠፋው ሕይወት በዚህ ሕይወት ግዳጅነታቸው ራሳቸውን እንዴት እንደሚመሩና የጽድቅ ጠባ ለማበጀት እጅግ የጠበቀ ቅንነት የሚያስፈልጋቸው መሆኑን አያስቡም፡፡ አለመታመንን ተንኮልን እያሰቡ የማይታመኑ መሆናቸውንም ይገልጻሉ፡፡ የወዲቱ ይዞታቸው የማጠፋው ሕይወት በዚሀ ሕይወት ግዳጅነታቸው ራሳቸውን እንዴት እንደሚመሩና የጽድቅ ጠባይ ለማበጀት እጅግ የጠበቀ ቅንነት የሚያስፈልጋቸው መሆኑነ ኤቡም፡፡ አለመታመን እውነትን እናምናለን በሚሉት ዘንድ የለብነታቸው ምክንያት ነው፡፡ እነሱ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት የላቸውምና የገዛ ነፍሳቸውንም ያታልላሉ፡፡ በሰንበት ጠባቂዎች መኻከል የሚሰቅቅ የመታመን ጉድለት እንዳለ ንግግር ሳደርግ እሳቀቃለሁ፡፡ 64T309-311;CCh 158.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents