Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፳፬—የጸሎት ስብሰባ፡፡

    የጸሎት ስብሰባዎች ከሚካሔዱት ስብሰባዎች እጅግ የሚያስደስቱ መሆን አለባቸው ፤ ነገር ግን እነዚህ ዘወትር ባለተገባ ሁናቴ የሚካሔዱ ናቸው፡፡ ብዙዎች ለስብከት ይገባሉ፤ ነገር ግን የጸሎትን ስብሰባ ችላ ይላሉ፡፡ እዚህ ላይ እንደገና ማሰብ የሚያስፈልግ ነው፡፡ ጥበብ ከአምላክ ሊፈልግ ይገባል፤ የሚያስደስቱና የሚስቡ እንዲሆኑ ስብሰባዎችን ለመምራት እቅዶች ሊታቀዱ አለባቸው፡፡ ሰዎች ለሕይወት እንጀራ ይራባሉ፡፡ በጸሎት ስብሰባ ቢያገኙት ሊቀበሉት እዚያ ይሔዳሉ፡፡CCh 164.1

    ረዘም ያሉ የሚያሰለቹ ንግግሮች በማናቸውም ሥፍራ ከሠፍራ ውጭ ናቸው፤ በተለይም በማሕበራዊ (በሶሺያል) ስብሰባ፡፡ ቀልጣፋዎች የሆኑና ለመናገርም ዝግጁዎች የሆኑ ፈሪዎቹንና አፋራሞቹን ምስክርነት እንዲያቀርቡ መጐስጐስ ይፈቀድላቸዋል፡፡ እጅግ አፈ ብልጦች የሆኑ ወትሮውንም ብዙ የሚሉት አላቸው፡፡ ጸሎታቸው ረዘም ያለና እንደ መኪና ነው፡፡ እነሱ መላእክትንና የሚያዳምጡቸውንመ ሰዎች የሚያሰለቹ ናቸው፡፡ ጸሎታችን አጠር ያለና ሐሳቡም የቀና መሆን አለበት፡፡ ረዘም ያሉና የሚያሰለቹ ልመናዎችን ማናቸውም እንዲህ ያለውን የሚያቀርቡ እንዳላቸው በክፍላቸው ውስጥ መተው አለባቸው፡፡ ያምላክ መንፈስ በልባቸው ውስጥ እስቲ ይግባ፤ ድርቅ ያለው መልክ የያዘውን ሁሉ ያስወግደዋል፡፡ ፩14T70, 71;CCh 164.2