Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የጉባዔ ጸሎት ረዘም ያለ መሆን የለበትም፡፡

    ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎታቸው አጠር ያለ ፤ የፈለጉትን ብቻ የሚገልጽ ከዚህም በቀር ሌላ እንዳይሆን አሳሰባቸው፡፡ ለሥጋዊና ለመንፈሳዊ በረከቶች ፍላጎታቸውን እየገለጹ ለዚሁ ምስጋናቸውን እንዲያቀርቡ የጸሎታቸውን ርዝመትና ዓይነት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ዓይነተኛ ጸሎት ምንኛ የተስተዋለ ነው፤ የሁሉንም የተረጋገጠ ፍላጎት የሚጠቀልል ነው፡፡ አንድ ወይም ሁለት ደቂቃዎች ለማናቸውም ለተለመደው ጸሎት በቂ ነው፡፡ ልመና በመንፈስ በሚቀርብበት ጸሎት በልዩ አኳኋን በእግዚአብሔር መንፈስ የሚነገርበት ጊዜያት ይኖራሉ፡፡ ናፋቂው ነፍስ ይጨነቅና ወደ አምላክ ያለቅሳል፡፡ ያዕቆብ እንዳደረገ መንፈስ ይታገላል፤ ልዩ የእግዚአብሔር ገለጻዎች ሳይታዩበት አያርፍም፡፡ ይህ አምላክ እንደሚፈልገው ያለ ነው፡፡CCh 164.3

    ነገር ግን ብዙዎች ጸሎትን በደረቁ በሰበካ አኳኋን ያቀርባሉ፡፡ እነዚህ የሚጸልዩ ወደ ሰዎች ነው እንጂ ወደ አምላክ የሚጸልዩ አይደለም፡፡ ወደ አምላክ የሚጸልዩ ቢሆንና የሚያደርጉትን በእርግጥ (በውነቱ) አስተውለው ቢሆን ኑሮ ፤ ስለ ድፍረታቸው በደነገጡ ነበር፤ የዓለማት (የዩንቨርስ) ፈጣሪ በዓለም ስለሚሆኑት ነገሮች ለጠቅላላ ጥያቄዎች እንፎርሜሺን እንዳስፈለገው አድርገው በጸሎት መልክ ለአምላክ ዲስኩር መስጠታቸው ነውና፡፡ እንዲህ ያሉ ጸሎቶች ሁሉ እንደሚጮህ ነሐስና እንደሚቃጭል ጸናጽል ናቸው፡፡ በሰማይ ከማንም የሚቆጠሩ አይደለም፡፡ ሟቾች ሰዎች እነሱን ለመስማት የተገደዱት እንደ ሰለቹዋቸው መላእክትም ይሰለቹዋቸዋል፡፡CCh 164.4

    የሱስ ብዙ ጊዜ በጸሎት ላይ ይገኝ ነበር፡፡ ልመናዎቹን ለአባቱ ያስታውቅ ዘንድ ብቻውን ወደ ደኖች ወይም ወደ ተራሮች ይሔድ ነበር፡፡ የቀን ሥራና ክብከባ ሲፈጸም የደከሙትም ዕረፍት ሲሹ ፤ የሱስ ጊዜውን ለጸሎት ቀድሶ ይሰጥ ነበር፡፡ በጸሎት ተስፋ አንቆርጥም እጅግ ያነሰ ጸሎት እንጸልይና ለዚሁ እንጠባበቃለንና፤ በመንፈስና በማስተዋል ረገድ ደግሞ ያነሰ ጸሎት እንጸልያለን፡፡ የጋለና ፍሬያማ ጸሎት ሁልጊዜ በሥፍራው ነው፤ ከቶውንም አይሰለችም፡፡ እንዲህ ያለ ጸሎት ያስደስታል፤ ለቅድስና (ለጸሎት) ፍቅር ያላቸውንም ሁሉ ያለመልማል፡፡CCh 165.1

    ምሥጢራዊ ጸሎት ችላ ተብሎዋል ፤ ስለዚህም ነው ብዙዎች እግዚአብሔርን ያመልኩ ዘንድ ሲሰበሰቡ እንዲህ ያለ ረዘም ያለ አሰልቻች የሆነ ቀዝቃዛ ጸሎት የሚጸልዩ፡፡ ሳምንቱን ችላ ስላሉት ተግባሮች ጸሎታቸውን ይደጋግማሉ፤ ችላ ያሉትን ለማቃናትና የሚገርፋቸውንም የተፈረደበትን (የተዘለፈውን) ሕሊናቸውን ለማረጋጋት ተስፋ አድርገው ደጋግመው ይጸልያሉ፡፡ አምላክ በሞገሡ እንዲቀበላቸው ለራሳቸው ለመጸለይ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን እኒህ ጸሎቶች በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ወደ ራሳቸው ዝቅተኛ ደረጃ የሌሎችን ሐሳቦች ወደ ማምጣት ዘወትር ውጤት ለሚያስገኝ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ስለ መትጋትና ስለ ጸሎት የክርስቶስን ትምህርቶች ቢቀበሉ ኑሮ እግዚአብሔርን በማምለካቸው በይበልጥ አስተዋዮች ይሆኑ ነበር፡፡ ፪22 T581, 582; CCh 165.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents