Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በጸሎት በይበልጥ ምሥጋና ማቅረብ፡፡

    «እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን” ፡፡ ምን ያህልስ ልናመሰግነው እንዳለብን ከኛ ማንኛችንም እንደሚገባ አስበንበታልን? ያምላክ ምሕረቶች በየጧቱ አዲሶች እንደሆኑና ታማኝነቱም ቅር የማያሰኝ መሆኑን እናስተውላለንን? እምነታችንን በርሱ ላይ እየጣልን እናስታውቃለንን? ለሞገሦቹ ሁሉ ምሥጋና እናቀርብለታለንን? ባንድ በኩል እኛ ብዙ ጊዜ፤ «በጎ ሥጦታ ሁሉ ፍጹምም አሰጣት ሁሉ ከላይ ነው ከብርሃናት አባት ወርዶ” የሚለውን እንረሳለን፡፡CCh 165.3

    በጤንነት ያሉ ዕለት ዕለት ፤ ዓመት ካመትም የሚቀጥሉትን አስደናቂ ምሕረቶቹን ምንኛ ብዙ ጊዜ ይረሱታል፡፡ በሰጣቸው ጥቅሞቹ ሁሉ የምሥጋና ውዳሴ አያቀርቡለትም፡፡ ነገር ግን በሽታ ሲይዛቸው አምላክ ይታሰባል፤ ለመዳንም ብርቱ ፍላጎት ስላላቸው አጥብቀን ወደ መጸለይ ይመራቸዋል፤ ይህም የቀና ነው፡፡ እግዚአብሔር በጤንነት ሳለንም ሆነ በሽታ ሲይዘንም መጠጊያችን ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎች ጉዳያቸውን ለርሱ አይተውትም፤ ስለ ራሳቸው በመስጋት ድክመትንና በሽታን ያደፋፍራሉ፡፡ መውቀስን ትተው በትካዜና በጨለማ ላይ ብድግ (ቢነሱ) ቢሉ መዳናቸው በጣም የተረጋገጠ ይሆንላቸዋል፡፡ በጤንነት በረከት ምን ያህል ጊዜ እንደተደሰቱበት በምሥጋና ማስታወስ አለባቸው፤ ይህም ክቡር በረከት ቢመለስላቸው ፤ ለፈጣሪያቸው እንደገና በታደሱላቸው ግዳጆች በታች መሆናቸውን መርሳት የለባቸውም፡፡ አሥሩ ለምጻሞች በተፈወሱ ጊዜ አንድ ብቻ የሱስን አግኝቶ ምስጋና ይሰጠው ዘንድ ተመለሰ፡፡ እንግዲህ እንደማያስቡት ዘጠኙ ልባቸው በአምላክ ምሕረት እንዳልተነኩት አንሁን፡፡ ፫35T315;CCh 165.4

    ባለፉት ክፉ ድርጊቶች ላይ የማሰላሰል ልምድ ጥሩ ያልሆነና ክርስቲያናዊ ሥራ አይደለም፡፡ እንዲህ በማድረጋችን በረከቶችን ሳንደሰትባቸውና ያሁኑን ምቹ ጊዜያቶች ሳናሻሽላቸው እንቀራለን፡፡ እግዚአብሔር የዛሬውን ተግባሮች እንድናደርግና ፈተናዎቹን እንቀበል ዘንድ ይፈልገናል፡፡ በቃል ወይም በምግባር እንዳንበድል ዛሬ መትጋት አለብን፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር ይገባናል፡፡ በሕያው (በጋለ) ሃይማኖት ምግባርን በማከናወን ዛሬ ጠላትን ማሸነፍ አለብን፡፡ ዛሬ እግዚብሔርን መሻት ይገባናል፤ እርሱ አብሮን ካልሆነ ተደሳቾች ሁነን የማናርፍ መሆናችንን ቁርጥ ሐሳብ ማድረግ አለብን፡፡ ይህ የተሰጠን የመጨረሻ ቀን መሆኑን በመገንዘብ መትጋት መሥራትና መጸለይ አለብን፡፡ እንግዲህ ሕይወታችን እንደምን እጅግ ጥብቅ የሆነ ነው፡፡ በቃሎቻችንና በአድራጎታችን ሁሉ የሱስን እንደምን በመቀራረብ መከተል ይኖርብናል፡፡CCh 166.1