Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በትንንሾቹ ነገሮች ያምላክ መደሰት (አሳቢነት)፡፡

    ክቡር የሆነውን የጸሎት መብት እንደሚገባ የሚወዱና የሚያሻሽሉ ጥቂቶች አሉ፡፡ ወደ የሱስ ሒደን ፍላጎታችንን ሁሉ መናገር አለብን፡፡ ትናንሹን ጣጣዎቻችንንና ብስጭቶቻችንን እንደዚሁም ትላልቅ መከራዎቻችንን ለርሱ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ እኛን ለማሸበር ወይም ለማስቸገር የሚነሳብንን ሁሉ በጸሎት ለጌታ ማቅረብ አለብን፡፡ በየእርምጃው የክርስቶስ አብሮን መሆን እንደሚያስፈልገን ሲሰማን ፤ ሰይጣን ፈተናዎቹን ጣልቃ ለማግባት ትንሽ ምቹ ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ከታላቁ እጅግ ርህሩህ ከሆነው ወዳጃችን ሊያርቀን የተጠና ጥረቱ ነው፡፡ የምንታመንበት ከየሱስ በቀር ማንንም ማድረግ የለብንም፡፡ በልባችን ውስጥ ስላለው ሁሉ ከርሱ ጋር በደህና ለመነጋገር እንችላለን፡፡CCh 166.2

    ወንድሞቼና እህቶቼ ለማህበራዊ (ለሶሽያል) ጸሎት ስትሰበሰቡ የሱስ እንደሚገናኛችሁ እመኑ፤ ሊባርካችሁም ፈቃደኛ መሆኑን እመኑ፡፡ ዓይንን ከራስ ወዲያ አዙሩ ወደ የሱስ ተመልከቱ ፤ ወደርም ስለሌለው ፍቅሩ ተነጋገሩ፡፡ እሱን በመመልከት ወደርሱ ተመሳሳይነት ትለወጣላችሁ፡፡ ስትጸልዩ አጠር ያለ ይሁን፤ ቀጥ ያለ ሐሳብ ይኑራችሁ፡፡ ረዘም ያለው ጸሎታችሁ ለጌታ ስብከት አትስበኩ፡፡ የራበው ልጅ ከምድራዊ አባቱ እንጀራን እንደሚለምነው፤ ለሕይወት እንጀራ ለምኑት፡፡ በገርነትና በሃይማኖት ብንለምንው ጌታ ተፈላጊውን በረከት ሁሉ ይሰጠናል፡፡CCh 166.3

    ጸሎት እጅግ የተቀደሰ የነፍስ ልምምድ ነው፡፡ ከልብ በትህትናና በጽናት መሆን አለበት ፤ማለት የታደሰው ልብ ምኞቶች በቅዱሱ አምላክ ፊት የተተነፈሱ መሆን አለባቸው፡፡ ለማኙ በአምላክ ፊት መሆኑ ሲሰማው ፤ ራስ ይረሳል፡፡ ሰብዓዊ መክሊትን ለማሳየት ፍላጎት የለውም፤ የሰዎችን ጆሮ ለማስደሰት አይሻም፤ ግን ነፍስ የሚፈልገውን በረከት ሊያገኝ እንጂ፡፡ ፭5GW 178.CCh 166.4

    በጉባዔም ሆነ በግል ጸሎት ለርሱ ልመናዎቻችንን ስናቀርብ በጌታ ፊት በጉልበታችን መንበርከክ መብታችን ነው የሱስ ምሳሌያችን ፤ «በጉልበቱም ተምበረከከና ጸየለ” (ሉቃስ ፳፪ ፡ ፵፩)፡፡ ስለ ደቀመዛሙርቱም ደግሞ «ተንበርክከው እንደ ጸለዩ” ይወሳል፡፡ (የሐዋ ፱ ፡ ፵፤ ምዕ ፳ ፡ ፴፮ ፤ ምዕ ፳፩፡ ፭)፡፡ ጳውሎስ «ስለዚህም በጉልበቴ እምበረከካለሁ ወደ ጌታችን ወደ ክርስቶስ አብ» ሲል ተናገረ፡፡ (ኤፌ ፫፡፲፬)፡፡ ስለ እሥራኤል ኃጢአት በአምላክ ፊት ሲናዘዝ ዕዝራ ተንበረከከ፤ (ዕዝራ ፱፡ ፭ን እይ)፡፡ ዳንኤል በጉልበቱም ተንበርክኮ በቀን ሶስት ጊዜ ይጸልይና ያመሰግን ነበር በአምላኩ ፊት (ዳንኤል ፮፡፲) ፡፡CCh 167.1

    * * * * *

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents