Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፬—የእግዚአብሔር የረተቀደስን ሰንበት መጠበቅ፡፡

    ሰንበትን በመጠበቅ ታላቅ በረከት ይገናል ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበት ቀን የደስታ ቀንአንዲሆንልን ይፈልጋል፡፡ ሰንበት በተደነገገ ጊዜ ደስታ ሁኖ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የእጆቹን ሥራ በደስታ ተመለከተ፡፡ የፈጠራቸው ሁሉ፣ ‹‹እጅግ መልካም ሆነ›› ሲል ተናገረ፡፡ ዘፍጥረት ፩፡፴፬፡፡ ሰማይና ምድር በደስታ ተመሉ፡፡ ‹‹የማልዶ አጥቢያ ኮከቦች አንድ ሁነው ባመሰገኑ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆችም ደስ ባላቸው ጊዜ››፡፡ ኢዮብ ፴፰፣፯፡፡CCh 43.1

    ኃጢአት ፍጹም የሆነው ሥራውን ለማበላሸት ወደ ዓለም ቢገባም በቸርነቱና በምሕረቱ ወሰን የሌለው ሁሉን የሚችል አምላክ ሁሉን ነገሮች መፍጠሩን ለምስክርነት ደግሞ ሰንበቱን ሰጠን፡፡ ሰማያዊ አባታችን፣ ሰንበትን በመጠበቃቸው ስለ ራሱ እንዲያውቁት በሰዎች መኻከል እውቀትን ይጠብቅ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ እውነተኛና ሕያው አምላክ መሆኑን፣ እርሱንም በማወቃችን ሕይወትንና ሰላምን የምናገኝ ለመሆናችን ሰንበት ሐሳባችንን ወደ እርሱ እንዲመራን ይፈልጋል፡፡CCh 43.2

    ጌታ ሕዝቡን እሥራኤልን ከምሥር ባወጣቸው ጊዜና ሕጉን በሰጣቸው ጊዜ ሰንበትን በመጠበቃቸው ከጣዖተኞች የተለዩ መሆናቸውን አስታወቃቸው፡፡ እግዚአብሔርን ገዥነት ባወቁትና ፈጣሪያቸውና ንጉሳቸው መሆኑን ለመቀበል ባልፈቀዱት መኻከል ልዩነትን ያመለክት የነበረው ይህ ነበር፡፡ ‹‹በኔና በእሥራኤል መኻከል የዘላለም ምልክት ነው›› ሲል ጌታ ተናገረ፣ ‹‹የእሥራኤልም ልጆች የሰንበትን ቀን ይጠብቁ በሰንበት ያርፉ ዘንድ ለልጅ ልጃቸው በዘላለም ኪዳን›› ዘፀዓት ፴፩፣፲፯፣፲፮፡፡CCh 43.3

    እሥራኤል ወደ ምድራዊ ከንዓን ይገቡ ዘንድ፣ ከምሥር በወጡ ጊዜ፣ ሰንበት የለያቸው ምልክት እንደ መሆኑ መጠን፣ አሁንም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወደ ሰማያዊ እረፍት ይገቡ ዘንድ ከዓለም ሲወጡ የሚለያቸው ምልክት ነው፡፡ ሰንበት በእግዚአብሔርና በሕዝብ መኻከል ስላለው ግንኙነት፣ሕጉንም የሚያከብሩ መሆናቸውን የሚያመለክት ምልክት ነው፡፡ በታዛዦቹ ዜጎቹና በሕግ ተላላፎች መኻከል ይለያል፡፡CCh 43.4

    ከደመናው ዓምድ ክርስቶስ ስለ ሰንበት፣ ‹‹ሰንበቶቼን ፈጽማችሁ ጠብቁ፡፡ በኔና በላንተ መኻከል ምልክት ነውና ለልጅ ልጃችሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር የምቀድሳችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ›› ሲል ተናገረ፡፡ ዘፀዓት ፴፩፣፲፫ ሰንበት እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑን የሚያመለክት ምልክት ሆኖ ለዓለም እንደ ተሰጠው፣ የሚቀድስም አምላክ መሆኑን ደግሞ የሚያመለክት ምልክት ነው፡፡ ሁሉን ነገሮች የፈጠረ ኃይል በርሱ አምሳል ነፍስን እንደገና የሚፈጥር ኃይል ነው፡፡ ሰንበትን በቅድስና ለሚጠብቁ የመቀደስ ምልክት ነው፡፡ እውነተኛ ቅድስና ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት፣ በጠባይም ከርሱ ጋር አንድ መሆን ነው፡፡ ይኸውም የጠባዩ ቅጅ ለሆኑት ሥርኣቶች (ፕርንስፕልስ) በመታዘዝ የሚገኝ ነው፡፡ ሰንበትም የመታዘዝ ምልክት ነው፡፡ ከልቡ አራተኛውን ትእዛዝ የሚታዘዝ ሕግን ሁሉ ይታዘዛል፡፡ እርሱ በመታዘዝ ይቀደሳል፡፡CCh 43.5

    ለእሥራኤልም ሆነ ለኛ ሰንበት ‹‹ለዘላለም ኪዳን›› የተሰጠ ነው፡፡ የተቀደሰውን ቀን ሰንበቱን ለሚያከብሩት፣ እግዚአብሔር የተመረጠ፣ ሕዝቡ መሆናቸውን ሚያውቅላቸው ለመሆኑ ምልክት ነው፣ ቃል ኪዳኑንም የሚፈጽምላቸው መሆኑን የሚያቀበል ነፍስ ሀሉ በመለኮታዊ ቃል ኪዳን በታች ፣ ራሱን ፣ ያኖራል ከወርቃቂ የመታዘዝ ሠንሰለት ፣ በየቀለበቱ ላይ ተስፋ ካለበት ፣ ጋር ራሱን ያቆራኛል ” ፩፤16 T349;350;CCh 44.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents